ዘፍጥረት 36:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦሆሊባማም የዑሻን፥ ያዕላምንና ቆሬን ወለደችለት። እነዚህ ሁሉ ለዔሳው በከነዓን ምድር የተወለዱለት ልጆች ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደዚሁም ኦሆሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኦሆሊባማም የዑሽን፥ ያዕላምን፥ ቆሬን ወለደች። በከነዓን ምድር የተወለዱለት የዔሳው ልጆች እነዚህ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤሌባማም ዮሔልን፥ ይጉሜልን፥ ቆሬንም ወለደች። በከነዓን ምድር የተወለዱለት የዔሳው ልጆች እነዚህ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አህሊባማም የዑስን የዕላምን፥ ቆሬን ወለደች፤ በከነዓን ምድር የተወለዱለት የዔሳው ልጆች እነዚህ ናቸው። |
ከዔሳው ሚስት ከኦሆሊባማ የተወለዱት የነገድ አለቆች፦ የዑሽ፥ ያዕላምና ቆሬ ናቸው፤ እነዚህ ከዐና ልጅ ከኦሆሊባማ የተወለዱ የዔሳው ትውልድ የነገድ አለቆች ናቸው።
ከዚህ በኋላ ዔሳው ሚስቶቹን ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፥ በቤቱ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ መንጋዎቹንና ሌሎቹንም ከብቶች ሁሉ፥ በከነዓን ሳለ ያፈራውን ንብረት ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።