ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።
ዘፍጥረት 36:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሳው ከነዓናውያን ሴቶችን አገባ፤ እነርሱም የሒታዊው የኤሎን ልጅ ዓዳ፥ የሒዋዊው የጺባዖን ልጅ ዐና የወለዳት ኦሆሊባማን እና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሳው ከከነዓን ሴቶች አገባ፤ እነርሱም፦ የኬጢያዊው የኤሎን ልጅ ዓዳን፣ የኤዊያዊው የፂብዖን ልጅ ዓና የወለዳት ኦሆሊባማ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፥ የኬጢያዊውን የዔሎንን ልጅ ዓዳን፥ የሒዋዊው የፅብዖን ልጅ ዓና የወለዳትን ኦሆሊባማን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ የኬጤያዊውን የዔሎን ልጅ ሐዳሶን፥ የኤውያዊው የሴቤሶ ልጅ ሐና የወለዳትን ኤሌባማን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሳው ከከነዓን ልጆች ሚስቶችን አገባ፤ የኬጢያዊውን የዔሎንን ልጅ ዓዳን የኤዊያዊው የፅብዖን ልጅ ዓን የወለዳትን አህሊባማም፥ |
ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።