ዘፍጥረት 34:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቱንም “ከዚህች ልጅ ጋር አጋባኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፣ “ይህችን ልጅ አጋባኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፥ “ይህችን ልጅ አጋባኝ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፥ “ይህችን ብላቴና አጋባኝ” ብሎ ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፦ ይህችን ብላቴና አጋባኝ ብሎ ነገረው። |
ያዕቆብ ልጁ ዲና ክብረ ንጽሕናዋ እንደ ተደፈረ ሰማ፤ ነገር ግን ወንዶች ልጆቹ የከብት መንጋ ይዘው ተሰማርተው ስለ ነበር፥ እነርሱ እስከሚመጡ ዝም ብሎ ቈየ፤
እንደዚህ ካዋረድከኝ በኋላ በሕዝብ ፊት ራሴን ቀና አድርጌ ለመሄድ እንዴት እችላለሁ? አንተም ብትሆን በእስራኤል እጅግ የተዋረድክ ትሆናለህ፤ ይልቅስ ለንጉሡ ብትነግረው እኔን ለአንተ በሚስትነት እንደሚሰጥህ እርግጠኛ ነኝ” አለችው።
ወደ ቤቱም ተመልሶ ለአባቱና ለእናቱ “በቲምና ከፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች አንድዋን አይቼ ወድጃታለሁ፤ ስለዚህ እርስዋን አጭታችሁ አጋቡኝ” አላቸው።