ዘፍጥረት 34:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዕለታት አንድ ቀን ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ዲና በዚያ አካባቢ የሚኖሩትን ከነዓናውያት ሴቶች ለማየት ወጣች፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ሴት ልጅ ዲና፣ አንድ ቀን የዚያን አገር ሴቶች ለማየት ወጣች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልያ ልጅ ዲናም፥ የዚያን አገር ሴት ልጆችን ለማየት ወጣች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለያዕቆብ የተወለደች የልያ ልጅ ዲናም የዚያን ሀገር ሴቶች ልጆችን ለማየት ወጣች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለያዕቆብ የወለደችለት የልያ ልጅ ዲናም የዚያን አገር ሴቶች ልጆችን ለማየት ወጣች። |
ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።
ይስሐቅ ያዕቆብን እንደ መረቀውና ሚስት እንዲፈልግ ወደ መስጴጦምያ እንደ ላከው ዔሳው ተረዳ፤ ይስሐቅ ያዕቆብን ሲመርቀው፦ “ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ” ብሎ ያዘዘው መሆኑንም ሰማ፤
እነዚህ ወንዶች ልጆችና ሴቷም ልጅ ዲና በመስጴጦምያ ሳሉ ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ናቸው። ያዕቆብ ከልያ ያፈራቸው ልጆችና የልጅ ልጆች ሠላሳ ሦስት ናቸው።
ወደ ባዕዳን ሕዝብ አማልክት ዘወር በማለትሽ ራስሽን አቃለሻል፤ ከዚህ በፊት በአሦር ምክንያት ኀፍረት እንደ ደረሰብሽ አሁን ደግሞ በግብጽ ምክንያት ኀፍረት ይደርስብሻል።
ደግሞም ሥራ መፍታትን ይማራሉ፤ ሥራ መፍታት ብቻ ሳይሆን በየሰዉ ቤት እየዞሩ ሰውን የሚያሙ፥ በሰው ነገር የሚገቡና መናገር የማይገባቸውን የሚናገሩ ይሆናሉ።