ዘፍጥረት 31:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባም ይጋርሣሀዱታ ብሎ ጠራት፤ ያዕቆብም ገለዓድ ብሎ ሰየማት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባም ክምር ድንጋዩን ይጋርሠሀዱታ ብሎ ጠራው፤ ያዕቆብ ደግሞ ገለዓድ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም “ይጋር ሠሀዱታ” ብሎ ጠራት፥ ያዕቆብም “ገለዓድ” አላት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም፥ “ይህች የድንጋይ ክምር በእኔና በአንተ መካከል ምስክር ትሁን” አለው። ላባም “ወግረ ስምዕ” ብሎ ጠራት፤ ያዕቆብም እንዲሁ አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም ይጋር ሠሀዱታ ብሎ ጠራት ያዕቆብም ገለዓድ አላት። |
ቀጥለውም ወደ ገለዓድና በሒታውያን ግዛት ውስጥ ወዳለው ወደ ቃዴስ ዘለቁ፤ ከዚያም በኋላ ወደ ዳን፥ ከዳንም ወደ ምዕራብ ታጥፈው ወደ ሲዶና ሄዱ፤
እንደ ደመና በዙሪያችን የከበቡን እነዚህ ሁሉ ምስክሮች ስላሉን እኛ እንደ ሸክም የሆነብንን ነገር ሁሉ በእኛ ላይ የተጣበቀብንን ኃጢአት አስወግደን በፊታችንም ያለውን የሩጫ እሽቅድድም በትዕግሥት በመጽናት እንሩጥ።
የሮቤልና የጋድ ሕዝብም “ይህ መሠዊያ እግዚአብሔር ብቻ አምላክ ስለ መሆኑ ለሁላችን ምስክር ነው” አሉ፤ ከዚህም የተነሣ “ምስክር” ብለው ጠሩት።