ነገር ግን በዚያኑ ቀን ላባ ሸመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቊጣ ያለባቸውን ወንዶች ፍየሎችና ዝንጒርጒር የሆኑትን ነጭ ነጠብጣብ ያለባቸውን ሴቶች ፍየሎች መረጠ፤ እንዲሁም ጥቊር የሆኑትን በጎች ለየና ልጆቹ እንዲጠብቁአቸው አደረገ።
ዘፍጥረት 31:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁንም እግዚአብሔር ከአባታችን ወስዶ ለአንተ የሰጠህ ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ያዘዘህን ሁሉ አድርግ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከአባታችን ወስዶ ለአንተ የሰጠው ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የነገረህን ሁሉ አድርግ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም እግዚአብሔር ከአባታችን የነሣው ሀብት ሁሉ የእኛና የልጆቻችን ነው፥ እንግዲያውስ አሁንም፥ እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ፥ አድርግ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም እግዚአብሔር ከአባታችን የነሣው ይህ ሁሉ ሀብትና ክብር ለእኛና ለልጆቻችን ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ አድርግ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም እግዚአብሔር ከአባታችን የነሣው ይህ ሁሉ ሀብት ለእኛና ለልጆቻችን ነው፤ አሁንም እግዚአብሔር ያለህን ሁሉ አድርግ። |
ነገር ግን በዚያኑ ቀን ላባ ሸመልመሌ የሆኑትን ወይም ነቊጣ ያለባቸውን ወንዶች ፍየሎችና ዝንጒርጒር የሆኑትን ነጭ ነጠብጣብ ያለባቸውን ሴቶች ፍየሎች መረጠ፤ እንዲሁም ጥቊር የሆኑትን በጎች ለየና ልጆቹ እንዲጠብቁአቸው አደረገ።