ዘፍጥረት 27:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዔሳውም “አባቴ ሆይ! ምርቃትህ አንዲት ብቻ ናትን? እባክህ እኔንም መርቀኝ” እያለ ድምፁን ከፍ አድርጎ አለቀሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዔሳውም አባቱን፣ “አባቴ ሆይ፤ ምርቃትህ ይህችው ብቻ ናትን? እባክህ አባቴ፣ እኔንም መርቀኝ” አለው፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሳውም አባቱን አለው፦ “አባቴ ሆይ፥ በረከትህ አንዲት ብቻ ናትን? አባቴ ሆይ፥ እኔንም ደግሞ ባርከኝ።” ዔሳውም ቃሉን አንሥቶ አለቀሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሳውም አባቱን ይስሐቅን አለው፥ “አባቴ ሆይ፥ በረከትህ አንዲት ብቻ ናትን? አባቴ ሆይ፥ እኔንም ደግሞ ባርከኝ።” ዔሳውም ጮሆ አለቀሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሳውም አባቱን አለው፦ አባቴ ሆይ እኔንም ደግሞ ባርከኝ። ዔሳውም ቃሉን አንሥቶ አለቀሰ። |
ዔሳውም “እርሱ እኔን ሲያሰናክለኝ ይህ ሁለተኛው ነው፤ ያዕቆብ መባሉ ተገቢ ነው፤ ከዚህ በፊት ብኲርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ፤ ታዲያ፥ ለእኔ ያስቀረኸው ምንም ምርቃት የለምን?” አለው።
እንግዲህ እነዚህ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፤ አባታቸው በባረካቸው ጊዜ ለእያንዳንዱ ተስማሚ የሆነውን የበረከት ቃል የተናገረው በዚህ ሁኔታ ነበር።
አገልጋዮቼ ከልባቸው ደስታ የተነሣ ይዘምራሉ፤ እናንተ ግን ከልብ ሐዘን የተነሣ ታላቅሳላችሁ፤ ከመንፈስም ጭንቀት የተነሣ ዋይ፥ ዋይ ትላላችሁ።
በኋላም ዔሳው በረከትን እንደገና ለመቀበል በፈለገ ጊዜ ይህን በረከት እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ እያለቀሰ እንኳ ያንን በረከት ተግቶ ቢፈልግ ሊያገኘው አልቻለም። ለንስሓ ምንም ዕድል አላገኘም።