ዘፍጥረት 27:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የታላቁ ልጅዋን የዔሳውን የክት ልብስ ከተቀመጠበት ቦታ አውጥታ ለያዕቆብ አለበሰችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ርብቃ በቤት ያስቀመጠችውን የታላቁን ልጇን የዔሳውን ምርጥ ልብስ አንሥታ ለታናሹ ልጇ ለያዕቆብ አለበሰችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርብቃም ከእርሷ ዘንድ በቤት የነበረችውን የታላቁን ልጇን የዔሳውን መልካሙን ልብስ አመጣች፥ ታናሹን ልጇን ያዕቆብንም አለበሰችው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርብቃም ከእርስዋ ዘንድ በቤት የነበረውን የታላቁን ልጅዋን የዔሳውን መልካሙን ልብስ አመጣች፤ ለታናሹ ልጅዋ ለያዕቆብም አለበሰችው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርብቃም ከእርስዋ ዘንድ በቤት የነበረውን የታላቁን ልጅውን የዔሳውን መልካሙን ልብስ አመጣች ታናሹን ልጅዋን ያዕቆብንም አለበሰችው፤ |
ያዕቆብም ቀርቦ ሳመው። ይስሐቅ የያዕቆብን ልብስ ባሸተተ ጊዜ እንዲህ ሲል መረቀው፥ “እነሆ የልጄ መልካም ሽታ፥ እግዚአብሔር እንደ ባረከው የእርሻ ሽታ ነው፤
አባቱ ግን አገልጋዮቹን ጠርቶ እንዲህ አለ፦ ‘ቶሎ ብላችሁ ከሁሉ የበለጠውን ልብስ አምጡና አልብሱት! በጣቱ ቀለበት፥ በእግሩም ጫማ አድርጉለት!
“ረጃጅም ልብስ ለብሰው ወዲያና ወዲህ መዞርን፥ በገበያም የክብር ሰላምታ መቀበልን፥ በምኲራብ የክብር ወንበርን፥ በግብዣም የክብር ስፍራን ከሚወዱ ከሕግ መምህራን ተጠንቀቁ።