La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 26:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያኑ ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቆፈሩት ጒድጓድ ለይስሐቅ ነገሩት፤ “ውሃ አገኘን” ብለውም ነገሩት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ዕለት፣ የይሥሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቈፈሩት የውሃ ጕድጓድ ነገሩት፤ “ውሃ እኮ አገኘን!” አሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያም ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጡ፥ ስለ ቈፈሩአትም ጉድጓድ፦ “ውኃ አገኘን ብለው ነገሩት።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ቀን የይ​ስ​ሐቅ ሎሌ​ዎች መጡ፤ ስለ ቈፈ​ሩ​አ​ትም ጕድ​ጓድ፥ ውኃ አገ​ኘን ብለው ነገ​ሩት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚይም ቀን የይስሐቅ ሎሌዎች መጡ፥ ስለቋፈሩአትም ጕድጓድ፦ ውኃ አገኘን ብለው ነገሩት።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 26:32
7 Referencias Cruzadas  

ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጒድጓድ ቈፈሩ።


በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ተነሡና ተማማሉ፤ ይስሐቅ ካሰናበታቸው በኋላም በሰላም ሄዱ።


እርሱም የውሃውን ጒድጓድ “ሳቤህ” ብሎ ጠራው፤ ስለዚህም የከተማይቱ ስም እስከ ዛሬ “ቤርሳቤህ” እየተባለ ይጠራል።


ስንፍና ያደኸያል፤ ተግቶ መሥራት ግን ያበለጽጋል፤


ሰነፍ አንድ ነገር ለማግኘት አጥብቆ ይመኛል፤ ይሁን እንጂ አያገኝም፤ ትጉህ ሠራተኛ ግን የሚፈልገውን ሁሉ ያገኛል።


“ለምኑ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ ታገኛላችሁ፤ በር አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤