Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 26:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ይስሐቅ በዚያ መሠዊያ ሠራና ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ መኖሪያውንም እዚያ አደረገ፤ አገልጋዮቹም ሌላ ጒድጓድ ቈፈሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ይሥሐቅም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ፤ ድንኳንም ተከለ፤ አገልጋዮቹም በዚያ የውሃ ጕድጓድ ቈፈሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በዚያም መሠዊያን ሠራ የጌታንም ስም ጠራ፥ በዚያም ድንኳን ተከለ፥ የይስሐቅም አገልጋዮች በዚያ ጉድጓድ ማሱ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በዚ​ያም ለአ​ም​ላኩ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ፤ በዚ​ያም ድን​ኳን ተከለ፤ የይ​ስ​ሐ​ቅም ሎሌ​ዎች በዚያ ጕድ​ጓድ ማሱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በዚያም መሠዊያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ፥ በዚይም ድንኳን ተከለ፤ የይስሐቅም ሎሌዎች በዚያ ጕድጓድ ማሱ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 26:25
11 Referencias Cruzadas  

የምስጋና መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፤ ወደ አንተም እጸልያለሁ።


ስለዚህ አብራም ድንኳኑን ነቅሎ በኬብሮን የመምሬ የተቀደሱ የወርካ ዛፎች ወደአሉበት ስፍራ ለመኖር ሄደ፤ እዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።


ሙሴም መሠዊያ ሠርቶ “እግዚአብሔር የድል ሰንደቅ ዓላማዬ ነው” ብሎ ሰየመው፤


እግዚአብሔር ያዕቆብን “አሁን ተነሥተህ ወደ ቤትኤል ሂድና እዚያ ኑር፤ በዚያም ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድክ ጊዜ ለተገለጥኩልህ አምላክ ለእኔ መሠዊያ ሥራ” አለው።


እዚያም መሠዊያ ሠራና “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።


እግዚአብሔር ወዳመለከተው ቦታ በደረሱ ጊዜ አብርሃም መሠዊያ ሠርቶ እንጨቱን በላዩ ላይ ረበረበው፤ ልጁን ይስሐቅንም አስሮ ከእንጨቱ በላይ በመሠዊያው ላይ አጋደመው።


መሠዊያም ሠርቶበት የነበረው ነው፤ እዚያም አብርሃም እግዚአብሔርን አመለከ።


ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያን ሠራ፤ ንጹሕ ከሆኑት እንስሶችና ወፎች ሁሉ ከየዐይነቱ አንዳንድ ወሰደ፤ መሥዋዕት እንዲሆኑም ሁሉንም በመሠዊያው ላይ አቃጠላቸው።


ሤትም “ሄኖስ” የተባለውን ወንድ ልጅ ወለደ፤ ሰዎች የእግዚአብሔርን ስም መጥራት የጀመሩት በዚያን ጊዜ ነው።


በዚያኑ ቀን የይስሐቅ አገልጋዮች መጥተው ስለ ቆፈሩት ጒድጓድ ለይስሐቅ ነገሩት፤ “ውሃ አገኘን” ብለውም ነገሩት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios