La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 24:47 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔም ‘የማን ልጅ ነሽ?’ ብዬ ጠየቅኋት። እርስዋም ‘የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ የባቱኤል አባት ናኮር እናቱም ሚልካ ይባላሉ’ አለችኝ። ከዚህ በኋላ ጒትቻ በጆሮዋ ላይ፥ አንባሮቹንም በእጆችዋ ላይ አደረግሁላት፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ለመሆኑ ‘የማን ልጅ ነሽ’ ብዬ ጠየቅኋት። “እርሷም፣ ‘ሚልካ ለናኮር የወለደችለት፣ የባቱኤል ልጅ ነኝ’ አለችኝ። “ከዚያም ቀለበቱን አደረግሁላት፤ አምባሩንም በእጇ አስገባሁላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔም፦ ‘አንቺ የማን ልጅ ነሽ?’ ብዬ ጠየቅኋት። እርሷም፦ ‘ሚልካ ለናኮር የወለደችለት የባቱኤል ልጅ ነኝ’ አለች፥ ቀለበትም አደረግሁላት፥ ለእጆችዋም አምባሮች አደረግሁላት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም “አንቺ የማን ልጅ ነሽ? ንገ​ሪኝ” ብዬ ጠየ​ቅ​ኋት። እር​ስ​ዋም፥ “ሚልካ የወ​ለ​ደ​ች​ለት የና​ኮር ልጅ የባ​ቱ​ኤል ልጅ ነኝ” አለ​ችኝ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም፦ አንቺ የማን ልጅ ነሽ? ብዬ ጠየቅኍት። እርስዋም ሚልካ ለናኮር የወለደችለት የባቱኤል ልጅ ነኝ አለች፤ ቀለበትም አደረግሁላት ለእጆችዋም አምባሮች አደረግሁላት።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 24:47
9 Referencias Cruzadas  

ከወርቅና ከብር የተሠሩ ጌጣጌጦችን፥ እንዲሁም ልብስ አውጥቶ ለርብቃ ሰጣት፤ ለወንድምዋና ለእናትዋም በጣም ውድ የሆኑ ስጦታዎችን አውጥቶ ሰጣቸው።


በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙት ወይዛዝርት መካከል፥ የነገሥታት ሴቶች ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጠኛ ልብስ ተጐናጽፋ ከዙፋንህ በስተቀኝ ቆማለች።


ማስተዋል የጐደላት ቈንጆ ሴት፥ ውበትዋ በዐሣማ አፍንጫ ላይ እንደሚገኝ የወርቅ ጒትቻ ነው።