እዚያ በደረሰ ጊዜ ከከተማው ውጪ ባለ የውሃ ጒድጓድ አጠገብ ግመሎቹ ተንበርክከው እንዲያርፉ አደረገ፤ ሰዓቱም ሊመሽ ተቃርቦ፥ ሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚወጡበት ጊዜ ነበር፤
ዘፍጥረት 24:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከዚህም በኋላ ዛሬ ወደ ውሃው ጒድጓድ ስመጣ እንዲህ ብዬ ጸለይኩ፤ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ እባክህ የመጣሁበት ጉዳይ እንዲቃና አድርግልኝ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እኔም ዛሬ ወደ ውሃው ጕድጓድ ስደርስ እንዲህ ብዬ ጸለይሁ፤ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈቃድህ ቢሆን የመጣሁበትን ጕዳይ አቃናልኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬም ወደ ውኃው ምንጭ መጣሁ፥ እንዲህም አልሁ፦ ‘የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የምሄድበትን መንገዴን ብታቀናልኝ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዛሬም ወደ ውኃው ጕድጓድ መጣሁ፤ እንዲህም አልሁ፥ “የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የምሄድበትን መንገዴን ብታቀናልኝ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛሬም ወደ ውኃው ምንጭ መጣሁ እንዲህም አልሁ፦ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ ዛሬ የምሄድበትን መንገዴን ብታቀናልኝ፤ |
እዚያ በደረሰ ጊዜ ከከተማው ውጪ ባለ የውሃ ጒድጓድ አጠገብ ግመሎቹ ተንበርክከው እንዲያርፉ አደረገ፤ ሰዓቱም ሊመሽ ተቃርቦ፥ ሴቶች ውሃ ለመቅዳት የሚወጡበት ጊዜ ነበር፤
“ለጌታዬ ያለውን ታማኝነትና ዘለዓለማዊ ፍቅር የጠበቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በቀጥታ መርቶ ወደ ጌታዬ ዘመዶች ቤት ያመጣኝ እርሱ ነው” አለ።
ስለዚህ ላባ “አንተ እግዚአብሔር የባረከህ ሰው፥ ና ወደ ቤት እንሂድ፤ በውጪ የቆምከው ለምንድን ነው? በቤታችን ለአንተ ማረፊያ ስፍራ አለ፤ ለግመሎችህም ማደሪያ የተዘጋጀ ቦታ አለ” አለው።
እግዚአብሔር ጒዞአችንን እንዲያቃናልን፥ እኛንና ልጆቻችንን፥ እንዲሁም ንብረታችንን ሁሉ እንዲጠብቅልን በእርሱ ፊት ራሳችንን ዝቅ አድርገን እንለምነው ዘንድ በዚያው በአሀዋ ወንዝ አጠገብ ጾም ዐወጅኩ።
እነሆ፥ አሁንም የእኔን ጸሎት ስማ፤ አንተን ማክበር የሚወዱትን የሌሎችንም አገልጋዮችህን ጸሎት አድምጥ፤ ዛሬ ልሠራው ያቀድኩት ይሳካልኝ ዘንድ የንጉሠ ነገሥቱን ልብ በማራራት እርዳኝ።” እነሆ፥ እኔ በዚህ ጊዜ የንጉሠ ነገሥቱ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።
እነርሱም “እኛ የመጣነው ከመቶ አለቃው ከቆርኔሌዎስ ዘንድ ነው፤ እርሱ የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ የሚያከብረው እግዚአብሔርን የሚያመልክ ደግ ሰው ነው፤ አንተን ወደ ቤቱ አስጠርቶ የምትለውን እንዲሰማ ቅዱስ መልአክ ገልጦ ነግሮታል” አሉት።
አገልጋዩም “ቈይ! እስቲ በዚህች ከተማ በጣም የተከበረ አንድ የእግዚአብሔር ሰው አለ፤ እርሱ የሚናገረው ቃል ሁሉ በትክክል ይፈጸማል፤ ስለዚህም ወደ እርሱ እንሂድ፤ ምናልባትም አህዮቹን የት ማግኘት እንደምንችል እርሱ ሊነግረን ይችል ይሆናል” ሲል መለሰለት።