ሣራም አብርሃምን “ይህችን አገልጋይ ከነልጅዋ ወዲያ አባርልኝ፤ የዚህች አገልጋይ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አብሮ መውረስ አይገባውም” አለችው።
ዘፍጥረት 24:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጌታዬ ሚስት ሣራ በእርጅናዋ ዘመን ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፤ ጌታዬም ያለውን ሀብት ሁሉ ለዚሁ ልጅ አውርሶታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጌታዬ ሚስት ሣራ በስተርጅናዋ ወንድ ልጅ ወልዳለታለች፤ ጌታዬም ያለውን ሀብት ሁሉ ለልጁ ሰጥቶታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሣራም የጌታዬ ሚስት በእርጅናው ለጌታዬ ወንድ ልጅን ወለደች፥ የነበረውንም ሁሉ ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌታዬ የአብርሃም ሚስት ሣራም በእርጅናዋ ለጌታዬ ወንድ ልጅን ወለደች፤ የነበረውንም ሁሉ ሰጠው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሣራም የጌታዬ ሚስት በእርጅናዋ ለጌታዬ ወንድ ልጅን ወለደች፤ የነበረውንም ሁሉ ሰጠው። |
ሣራም አብርሃምን “ይህችን አገልጋይ ከነልጅዋ ወዲያ አባርልኝ፤ የዚህች አገልጋይ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አብሮ መውረስ አይገባውም” አለችው።
ዕድሜው መቶ ዓመት ያኽል ስለ ነበረ በሥጋው መድከም እንደ ሞተ በመሆን ምክንያት መውለድ እንደማይችልና ሣራም መኻንና ያረጀች በመሆንዋ መውለድ እንደማትችል ቢያውቅም በእምነቱ ደካማ አልሆነም።