ዘፍጥረት 23:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አብርሃም በሒታውያን ፊት እጅ ነሥቶ እንዲህ አለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አብርሃም ተነሥቶ የአገሬውን ሕዝብ፣ ኬጢያውያንን እጅ ነሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም፥ በሒታውያን ፊት እጅ ነሣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ተነሣ፤ በሀገሩ ሕዝብ ፊትም ለኬጢ ልጆች ሰገደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ተነሣ ለምድሩ ሕዝብም ለኬጢ ልጆች ሰገደ። |
ቀና ብሎም ሲመለከት ሦስት ሰዎች እዚያ ቆመው አየ፤ እንዳያቸውም ወዲያውኑ ሊያነጋግራቸው ወደ እነርሱ ሮጠ፤ ግንባሩም መሬት እስኪነካ ዝቅ ብሎ በመስገድ እጅ ነሣ፤
በዚያኑ ምሽት ሁለቱ መላእክት ወደ ሰዶም መጡ፤ በዚያን ጊዜ ሎጥ በከተማይቱ በር ተቀምጦ ነበር፤ መላእክቱን ባያቸው ጊዜ ሊያነጋግራቸው ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሄደ፤ ጐንበስ ብሎም እጅ ነሣቸውና፥
“ጌታው፥ እስቲ ስማን፤ አንተ በመካከላችን እንደ ታላቅ መስፍን ነህ፤ ከመቃብሮቻችን ጥሩውን መርጠህ የሚስትህን አስከሬን እዚያ ቅበር፤ ሁላችንም ብንሆን የሚስትህን አስከሬን የምትቀብርበት መቃብር ልንሰጥህ ፈቃደኞች ነን” አሉት።
በቀረውስ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ በመስማማት ኑሩ፤ የሌላውን ሰው ችግር እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ደጎችና ትሑቶች ሁኑ።