ዘፍጥረት 13:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአብራም ጋር ይጓዝ የነበረው ሎጥም በበኩሉ፥ ብዙ በጎች፥ ፍየሎችና ከብቶች፥ ድንኳኖችም ነበሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአብራም ጋራ ዐብሮት ይጓዝ የነበረው ሎጥ በጎች፣ ከብቶችና ድንኳኖች ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአብራም ጋር የሄደው ሎጥ ደግሞ የላምና የበግ መንጋ ድንኳንም ነበረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአብራም ጋር የሄደው ሎጥ ደግሞ የላምና የበግ መንጋ ድንኳኖችም ነበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአብራም ጋር የሄደው ሎጥ ደግሞ የላምና የበግ መንጋ ድንኳንም ነበረው። |
አብራም፥ ሚስቱ ሣራይና የወንድሙ ልጅ ሎጥ፥ በካራን ሳሉ ያገኙትን ሀብትና አገልጋዮቻቸውን ሁሉ ይዘው ወደ ከነዓን ምድር ሄዱ። ከነዓን በደረሱ ጊዜ፥
ከብቶቻቸውን በአንድነት የሚያሰማሩበት በቂ የግጦሽ ቦታ ስላልነበረና አብራምና ሎጥ ብዙ የከብት መንጋ ስለ ነበራቸው አብረው ለመኖር አልቻሉም፤
ድንኳኖቻቸውን፥ መንጋዎቻቸውን፥ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ሁሉ ውሰዱ፤ ግመሎቻቸውን ለራሳችሁ ውሰዱ። ‘በዙሪያው ሽብር ተነሥቷል’ ብለው ይጮኻሉ።”