La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 12:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን በአብርሃም ሚስት በሣራይ ምክንያት እግዚአብሔር በእርሱና በባለሟሎቹ ሁሉ ላይ አሠቃቂ በሽታዎች አመጣባቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ፈርዖንንና ቤተ ሰዎቹን በጽኑ ደዌ መታቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እግዚአብሔርም በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ፈርዖንንና የቤቱን ሰዎች በታላቅ መቅሠፍት መታ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ብ​ራም ሚስት በሦራ ምክ​ን​ያት ፈር​ዖ​ን​ንና የቤ​ቱን ሰዎች በታ​ላቅ መቅ​ሠ​ፍት መታ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ፈርዖንንና የቤቱን ሰዎች በታላቅ መቅሠፍት መታ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 12:17
8 Referencias Cruzadas  

ከዚያ በኋላ አብርሃም ለእግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም አቤሜሌክንና ሚስቱን፥ ሴቶች አገልጋዮቹንም ፈውሶአቸው ልጆች እንዲወልዱ አድርጎአቸዋል፤


በአብርሃም ሚስት በሣራ ምክንያት የአቤሜሌክ ቤተሰብን ማሕፀን ሁሉ ዘግቶ ነበር።


ነገር ግን አንድ ሌሊት እግዚአብሔር በሕልም ተገልጦ አቤሜሌክን “ይህች ሴት ባለባል ስለ ሆነች እርስዋን በመውሰድህ ምክንያት ትሞታለህ” አለው።


እግዚአብሔር ግን ማንም እንዲጨቊናቸው አልፈቀደም፤ ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ።


ዳዊትም “ቸነፈሩ ይወገድ ዘንድ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንድሠራበት አውድማህን ሽጥልኝ፤ እኔም ሙሉ ዋጋ እሰጥሃለሁ” አለው።


ሁሉም የእጁ ሥራዎች ስለ ሆኑ፤ እርሱ ለመኳንንቱ አያደላም ባለጸጋውን ከድኻው አይለይም።


ጋብቻ በሁሉ ዘንድ የተከበረ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን እግዚአብሔር ስለሚፈርድባቸው ባልና ሚስት ታማኝነትን በማጒደል ጋብቻን አያርክሱ።