ታራ ልጁን አብራምን፥ ከሃራን የተወለደውን የልጅ ልጁን ሎጥን፥ የአብራም ሚስት የሆነችውን ምራቱን ሣራይን ይዞ በባቢሎን የምትገኘውን የኡርን ከተማ በመተው ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ካራን ዘልቀው እዚያ ተቀመጡ።
ዘፍጥረት 11:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሃራን አባቱ ታራ ገና በሕይወት ሳለ በተወለደባት ከተማ በኡር ሞተ፤ ኡር የምትገኘው በከለዳውያን ምድር ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐራን፣ አባቱ ታራ ገና በሕይወት እንዳለ በከለዳውያን ምድር በምትገኘው በተወለደባት ከተማ በዑር ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐራንም በተወለደበት አገር በከለዳውያን ዑር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አራንም በተወለደባት ሀገር በከለዳውያን ምድር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐራንም በተወለደበት አገር በከለዳውያን ዑር በአባቱ በታራ ፊት ሞተ። |
ታራ ልጁን አብራምን፥ ከሃራን የተወለደውን የልጅ ልጁን ሎጥን፥ የአብራም ሚስት የሆነችውን ምራቱን ሣራይን ይዞ በባቢሎን የምትገኘውን የኡርን ከተማ በመተው ወደ ከነዓን ምድር ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ካራን ዘልቀው እዚያ ተቀመጡ።
ደግሞም እግዚአብሔር አብራምን “ይህችን አገር በውርስ ለአንተ እንድሰጥህ ዑር ከምትባለው ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው።
ይኸኛው መልእክተኛ ተናግሮ ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፥ “በሦስት ቡድን የተከፈሉ የከለዳውያን ዘራፊዎች በድንገት አደጋ ጣሉብን፤ ግመሎቹን በሙሉ ወሰዱአቸው፤ አገልጋዮችህንም በሙሉ በሰይፍ ገደሉአቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።