እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ ሕዝቦች የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።
ዘፍጥረት 11:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያ የዓለም ሕዝቦች መነጋገሪያ ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ሰዎች ሁሉ የሚናገሩትና የሚግባቡበት ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ ሰዎች ሁሉ የሚናገሩበትና የሚግባቡበት ቋንቋ አንድ ብቻ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዓለም ሁሉ ቋንቋ አንድ፥ ንግግሩም አንድ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድርም ሁሉ በአንድ ቋንቋና በአንድ ንግግር ነበረች። |
እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ ሕዝቦች የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።
እንዲህም አለ፤ “እነሆ፥ እነዚህ ሰዎች አንድ ወገን ናቸው፤ መነጋገሪያ ቋንቋቸውም አንድ ነው፤ ይህም ከሚሠሩት የመጀመሪያው ብቻ ነው፤ በዚህ ዐይነት ሊሠሩ ያቀዱትን ሁሉ ማድረግ አያቅታቸውም።
በዚያን ጊዜ በግብጽ ውስጥ የሚገኙ አምስት ከተሞች የዕብራውያን ቋንቋ ይናገራሉ፤ በዚያም የሚኖሩ ሕዝቦች በሠራዊት አምላክ ስም ይምላሉ፤ ከእነዚህ ከተሞች አንዲቱ “የፀሐይ ከተማ” ተብላ ትጠራለች።
“በዚያን ጊዜ ሕዝቦች ንጹሕ ንግግር እንዲናገሩ አደርጋለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ሁሉም የእኔን የእግዚአብሔርን ስም እንዲጠሩና በአንድነት እንዲያገለግሉኝ ነው።