ዘፍጥረት 10:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናምሩድ በእግዚአብሔር ድጋፍ ታላቅ አዳኝ ነበረ፤ ሰዎች “እንደ ናምሩድ ታላቅ አዳኝ ያድርግህ!” እያሉ የሚመርቁት ስለዚህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ዐዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፣ “በእግዚአብሔር ፊት እንደ ናምሩድ ብርቱ ዐዳኝ” ይባል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ፊት ናምሩድ ኃያል አዳኝ ነበረ፥ ስለዚህም፦ “እንደ ናምሩድ በጌታ ፊት ኃያል አዳኝ” ይባላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኀያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት ኀያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያክ አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም፥ በእግዚአብሔር ፊት ኃያክ አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ። |
በዚያን ዘመንና ከዚያም በኋላ ከሰዎች ሴቶች ልጆችና ከእግዚአብሔር ልጆች ተዳቅለው የተወለዱ “ኔፊሊም” የሚባሉ ግዙፎች ሰዎች ነበሩ። እነርሱ በጥንት ዘመን በጀግንነታቸው የታወቁ ዝነኞች ሰዎች ነበሩ።
ያቺ አገር መልእክተኞችን ከደንገል በተሠራ ጀልባ በአባይ ወንዝ ላይ ትልካለች፤ ሕዝብዋ ረጃጅሞችና ቆዳቸው ለስላሳ፥ አገራቸው በወንዞች የተከፋፈለች፥ ጠንካሮችና ኀያላን በመሆናቸው በዓለም ሁሉ ወደሚፈሩት ሕዝቦች እናንት ፈጣን መልእክተኞች ሂዱ!
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን ሕዝብ እንደ ዓሣ የሚያጠምዱና እንደ አውሬ የሚያድኑ ብዙ ሰዎችን እልካለሁ፤ በየተራራውና በየኰረብታው በቋጥኞች ውስጥ ባሉ ዋሻዎችም እያደኑ ይይዙአቸዋል።
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገራቸው፦ በጡንቻ ላይ የሚደረግ አሸን ክታብን ለሚሰፉ፥ የሰውንም ሕይወት ለማጥመድ በተለያየ ቁመት የራስ መሸፈኛ ሻሽ ለሚያዘጋጁ ሴቶች ወዮላቸው! ከእኔ ሕዝብ መካከል ሰዎችን አጥምዳችሁ እናንተ በሕይወት ትኖራላችሁን?
ከምድሪቱ ላይ ታማኝ ሰው ጠፍቶአል፤ አንድም ትክክለኛ ሰው የለም፤ ሁላቸውም ሰውን ለመግደል ያደባሉ፤ እርስ በርሳቸውም አንዱ ሌላውን ተከታትሎ ያጠምዳል።