እነዚህ ሁሉ በባሕር ዳርቻና በደሴቶች ላይ ለሚኖሩ የያፌት ዘሮች ቅድመ አያቶች ናቸው፤ በየአገራቸውና በየጐሣቸውም ተከፋፍለው የሚኖሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገርበት የራሱ ቋንቋ ነበረው።
ዘፍጥረት 10:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የካም ልጆች፦ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥና ከነዓን ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የካም ልጆች፦ ኵሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ፣ ከነዓን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የካም ልጆች፦ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ እና ከነዓን ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምስራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፋጥ፥ ከነዓን ናቸው። |
እነዚህ ሁሉ በባሕር ዳርቻና በደሴቶች ላይ ለሚኖሩ የያፌት ዘሮች ቅድመ አያቶች ናቸው፤ በየአገራቸውና በየጐሣቸውም ተከፋፍለው የሚኖሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገርበት የራሱ ቋንቋ ነበረው።
በዚያም ጸጥታና ሰላም በሰፈነበት ገላጣማ አገር ለም የሆነ የግጦሽ ቦታ በብዛት አገኙ፤ ቀደም ሲል በዚያ ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች ከካም ዘሮች ነበሩ።
በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።
ፈረሶች ወደ ፊት እንዲሄዱ፥ ሠረገሎችም አስደንጋጭ በሆነ ፍጥነት እንዲሽከረከሩ እዘዙ፤ ከኢትዮጵያና ከሊቢያ ጋሻቸውን አንግበው በመጡ ሰዎችና፥ ከልድያ በመጡ ቀስት በሚወረውሩ ኀያላን ሰዎች ጭምር የተጠናከሩ ወታደሮችን ላኩ” ይላል እግዚአብሔር።
“ከፋርስ፥ ከልድያና ከሊቢያ የመጡ ወታደሮች በሠራዊትሽ ውስጥ ያገለግላሉ፤ ጋሻቸውንና የራስ ቊራቸውን በጦር ሰፈርሽ ሰቅለዋል፤ እነርሱ ለአንቺ ክብር ያስገኙ ሰዎች ናቸው።