እነዚህ ሁሉ የካም ዘሮች ናቸው፤ እነርሱ በተለያዩ ጐሣዎችና አገሮች ተከፍለው ይኖሩ ነበር፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገረው በራሱ ቋንቋ ነበር።
ዘፍጥረት 10:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሁሉ በባሕር ዳርቻና በደሴቶች ላይ ለሚኖሩ የያፌት ዘሮች ቅድመ አያቶች ናቸው፤ በየአገራቸውና በየጐሣቸውም ተከፋፍለው የሚኖሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገርበት የራሱ ቋንቋ ነበረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነዚህም በባሕር ዳርቻ ሕዝቦች፥ ሁሉም በየምድራቸው፥ በየቋንቋቸው፥ በየነገዳቸው፥ በየሕዝባቸው ተከፋፍለው የሚኖሩ የያፌት ልጆች ዘር ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው፥ በየቋንቋቸው፥ በየነገዳቸው፥ በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ። |
እነዚህ ሁሉ የካም ዘሮች ናቸው፤ እነርሱ በተለያዩ ጐሣዎችና አገሮች ተከፍለው ይኖሩ ነበር፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገረው በራሱ ቋንቋ ነበር።
እነዚህ በየነገዳቸው የተከፋፈሉ ሕዝቦች የኖኅ ዘሮች ነበሩ፤ ከጥፋት ውሃ በኋላ የምድር ሕዝቦች ሁሉ የተገኙት ከእነዚህ ከኖኅ ልጆች ነበር።
በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።
በእግዚአብሔር ፊት ሕዝቦች እንደ አንድ የውሃ ጠብታ ናቸው፤ በሚዛንም ላይ እንዳለ ዐቧራ ናቸው፤ ደሴቶችም በእርሱ ዘንድ እንደ ትቢያ የቀለሉ ናቸው።
“በደሴቶች የሚኖሩ ሕዝቦች እኔ ያደረግኹትን ሁሉ አይተዋል፤ ስለዚህም እጅግ ደንግጠው ተንቀጥቅጠዋል፤ በአንድነትም ተሰብስበው ወደ እኔ መጥተዋል።
ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! በባሕሩ ውስጥ ያሉት ሁሉ፥ የጠረፍ አገሮችና በእነርሱም የሚኖሩ ሁሉ ያመስግኑ!
በምድር ላይ ፍትሕን እስኪመሠርት ድረስ እርሱ አይታክትም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ በሩቅ ያሉ ሕዝቦችም የእርሱን ትምህርት ለመስማት ይናፍቃሉ።”
በደሴት የምትኖሩ ሕዝቦች አድምጡኝ! በሩቅ አገር ያላችሁም ሰዎች አስተውሉ፤ እግዚአብሔር ከመወለዴ በፊት ጠራኝ፤ በእናቴ ማሕፀን እያለሁ ስም አወጣልኝ።
ፈጥኜ በመምጣት አድናቸዋለሁ፤ በቅጽበት ድል የምነሣበት ጊዜ ይመጣል፤ በኀይሌ ሕዝቦችን ሁሉ እገዛለሁ፤ በደሴቶች የሚኖሩ ሕዝቦች፥ እኔን በተስፋ ይጠባበቃሉ፤ ኀይሌንም ተስፋ ያደርጋሉ።
የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ስላከበራችሁ ለእርሱ ክብር ሲሉ በተርሴስ መርከቦች መሪነት ልጆቻችሁን ከብራቸውና ከወርቃቸው ጋር ከሩቅ ቦታ ለማምጣት ደሴቶቹ እኔን ይጠባበቃሉ።
ይህን የመሰለ ነገር ከዚህ በፊት ከቶ ተደርጎ እንደማያውቅ ታስተውሉ ዘንድ፥ እስቲ በስተ ምዕራብ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ሂዱ፤ በስተ ምሥራቅም ወደ ቄዳር ምድር መልእክተኞች ልካችሁ መርምሩ።
ልዑል እግዚአብሔር ለጢሮስ ከተማ እንዲህ ይላታል፦ “ቊስለኞች ሲቃትቱና በመካከልሽ ግድያ ሲካሄድ ባወዳደቅሽ ድምፅ የጠረፉ አካባቢ አይናወጥምን?
ከዚያ በኋላ በባሕር ጠረፍ ባሉት አገሮች ላይ አደጋ ጥሎ ከእነርሱ ብዙዎቹን ይይዛል፤ ነገር ግን አንድ የጦር መሪ ድል ስለሚነሣው የትዕቢቱ ፍጻሜ ይሆናል፤ በእርግጥም በትዕቢት የተናገረው ስድብ ሁሉ በእርሱ ላይ ይፈጸማል።
በምድራቸው ያሉትን ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በማጥፋቱ እግዚአብሔር በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በባሕር ጠረፍና በደሴቶች የሚኖሩ መንግሥታት ሁሉ በያሉበት ለእርሱ ይሰግዳሉ።
ልዑል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስታቸውን ባከፋፈለ ጊዜ፥ የሰውን ዘር በለያየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቊጥር ብዛት፥ ለሕዝቡ ድንበርን ሠራላቸው።