ዘፍጥረት 1:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “ብዙ፤ ተባዙ፤ ዘራችሁ ምድርን ይሙላ፤ ምድርም በቊጥጥራችሁ ሥር ትሁን፤ በባሕር ውስጥ በሚኖሩ ዓሣዎች፥ በሰማይ በሚበርሩ ወፎችና በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራችሁ” ብሎ ባረካቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ ግዟትም፤ የባሕርን ዓሦች፣ የሰማይን ወፎች፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ግዟቸው” ብሎ ባረካቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፥ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፥ “ብዙ፤ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም፤ የባሕርን ዓሣዎችንና የምድር አራዊትን፥ የሰማይ ወፎችንና እንስሳትንም ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ባረካቸዉ፤ እንዲህም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትም ሁሉ ግዙአቸዉ። |
እርስዋን እባርካታለሁ፤ ከእርስዋም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ እባርካታለሁ፤ የብዙ ሕዝቦችም እናት ትሆናለች፤ ከዘርዋም መካከል ነገሥታት የሚሆኑ ይገኛሉ።”
ስለ እስማኤል ያቀረብከውንም ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱንም እባርከዋለሁ፤ ብዙ ልጆችን እሰጠዋለሁ፤ ዘሩንም እጅግ አበዛዋለሁ፤ እርሱ የዐሥራ ሁለት መሳፍንት አባት ይሆናል፤ ዘሩንም ታላቅ ሕዝብ አደርገዋለሁ።
በዚያን ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ፤ እኔ ከአንተ ጋር ስለ ሆንኩ አትፍራ፤ ለአገልጋዬ ለአብርሃም በገባሁት ቃል ኪዳን መሠረት እባርክሃለሁ፤ ዘርህንም አበዛዋለሁ” አለው።
ዔሳው በዙሪያው ተመልክቶ ሴቶቹንና ልጆቹን ባየ ጊዜ “እነዚህ ሁሉ ከአንተ ጋር ያሉ ሰዎች የማን ናቸው?” አለ። ያዕቆብም “ጌታዬ ሆይ፥ እነዚህ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሰጠኝ ልጆች ናቸው” ሲል መለሰ።
የአባትህ አምላክ ይረዳሃል፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ከላይ ከሰማይ ዝናብን፥ ከምድርም ጥልቀት ውሃን በመስጠት ይባርክሃል፤ ብዙ ከብትና ብዙ ልጆችም ይሰጥሃል።
ተራብተውና ተባዝተው ምድርን ሁሉ እንዲሞሉ ከአንተ ጋር ያሉትን ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ወፎችን፥ እንስሶችንና ሌሎችን በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ፍጥረቶች ሁሉ ይዘህ ውጣ።”
ያዕቤጽም “አምላኬ ሆይ፥ ባርከኝ፤ ሰፊ ምድርንም ስጠኝ፤ እጅህ ከእኔ ጋር ይሁን፤ ሥቃይ ሊያስከትልብኝ ከሚችል ከማንኛውም ክፉ ነገር ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።
እግዚአብሔር የኢዮብን የመጨረሻ ሕይወት ከመጀመሪያው አስበልጦ ባረከው፤ ስለዚህ ኢዮብ ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፤ ስድስት ሺህ ግመሎች፤ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፤ አንድ ሺህ እንስት አህዮች ነበሩት።
ሰማያትን የፈጠረው እርሱ እግዚአብሔር ነው፤ ለምድር ቅርጽ ሰጥቶ የሠራት፥ የመሠረታትም እርሱ ነው፤ የፈጠራትም መኖሪያ እንድትሆን ነው እንጂ፥ ቅርጽ የሌላትና ባዶ እንድትሆን አይደለም፤ እርሱ፦ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤
እንደእነዚህ ያሉት ሰዎች ጋብቻን ይከለክላሉ፤ የሚያምኑና እውነትን የሚያውቁ ሰዎችም እርሱን እያመሰገኑ እንዲመገቡት እግዚአብሔር የፈጠረላቸውን ምግብ “አትብሉ” እያሉ ይከለክላሉ።