ገላትያ 6:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ ሰው የራሱን ሥራ መርምሮ ይፈትን፤ ከዚህ በኋላ ራሱን ከሌሎች ጋር በማወዳደር ሳይሆን ለራሱ ብቻ የሚመካበትን ነገር ያገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱ የራሱን ተግባር ይመርምር፤ ከዚያም በኋላ፣ ከሌላ ሰው ጋራ ራሱን ሳያወዳድር፣ ስለ ራሱ የሚመካበትን ያገኛል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እያንዳንዱ የገዛ ሥራውን ይፈትን፤ ከዚያም በኋላ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፥ ስለ ሌላው ግን አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሌላ ያይደለ ለራሱ መመኪያ እንዲሆነው ሁሉም ሥራዉን ይመርምር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፤ |
“ፈሪሳዊው ቆሞ እንዲህ ሲል በልቡ ጸለየ፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኔ እንደ ሌሎች ሰዎች ቀማኛ፥ ግፈኛ አመንዝራ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ፤ ይልቁንም እንደዚህ እንደ ቀራጭ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ።
የምንመካበት ነገር ይህ ነው፤ ይህም እውነት መሆኑን ኅሊናችን ይመሰክርልናል፤ ከሌሎች ሰዎችና በተለይም ከእናንተ ጋር የነበረን ግንኙነት ከእግዚአብሔር ባገኘነው ቅድስናና ቅንነት የተመሠረተ ነው፤ ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ጸጋ ነበር እንጂ በሰው ጥበብ አልነበረም።
በእምነታችሁ የጸናችሁ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ መሆኑን አልተገነዘባችሁምን? አለበለዚያ በፈተና ወድቃችኋል ማለት ነው፤