ከዚህም በኋላ እርስዋ ደብዳቤ ጽፋ በአክዓብ ስም ፈርማ የእርሱኑ ማኅተም አተመችበት፤ ደብዳቤውንም ናቡቴ ወደሚኖርባት ወደ ኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎች ላከች።
ዕዝራ 4:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደብዳቤውም ፍሬ ነገር ይህ ነው፤ በኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ከሚኖሩ አገልጋዮቹ ለንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ የተላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የላኩለት ደብዳቤ ቅጅ ይህ ነው፤ ለንጉሥ አርጤክስስ፣ በኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ከሚኖሩት አገልጋዮችህ የተላከ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም የላኩት የደብዳቤ ግልባጭ ይህ ነው፦ “ለንጉሡ ለአርጤክስስ፥ አገልጋዮችህ በወንዙ ማዶ ያለ አገር የሚኖሩ ሰዎች፤ አሁንም የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለንጉሡ ለአርተሰስታ የላኩት የደብዳቤ ቃልም ይህ ነው፥ “በወንዝ ማዶ ያሉት ሰዎች ባሪያዎችህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለንጉሡ ለአርጤክስስ የላኩት የደብዳቤ ግልባጭ ይህ ነው “በወንዝ ማዶ ያሉት ሰዎች ባሪያዎችህ፤ |
ከዚህም በኋላ እርስዋ ደብዳቤ ጽፋ በአክዓብ ስም ፈርማ የእርሱኑ ማኅተም አተመችበት፤ ደብዳቤውንም ናቡቴ ወደሚኖርባት ወደ ኢይዝራኤል ባለሥልጣኖችና ሽማግሌዎች ላከች።
የተመለሱት ምርኮኞች በምድሪቱ ከሚኖሩት አሕዛብ ተቃውሞ የተነሣ ፍርሀት ቢያድርባቸውም እንኳ መሠዊያውን በዚያው ቀድሞ በቆመበት ቦታ መልሰው ሠሩት፤ ከዚያም በኋላ የሚቃጠል መሥዋዕት ዘወትር ጠዋትና ማታ በዚያ ላይ እንደገና ማቅረብ ጀመሩ።
ታላቁና ኀያሉ ንጉሠ ነገሥት አሰናፈር ከየተወለዱበት አገር በማዛወር በሰማርያ ከተማና ከኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል በየአውራጃው እንዲሰፍሩ ካደረጋቸው ከሌሎችም ሕዝቦች ጋር በመተባበር የተጻፈ ሲሆን።
“ከግርማዊነትዎ ዘንድ የመጡት አይሁድ እዚህ ኢየሩሳሌም የደረሱ መሆናቸው በግርማዊነትዎ ዘንድ የታወቀ ይሁን። ያቺን ዐመፀኛና ክፉ ከተማ እንደገና በመሥራት ላይ ናቸው፤ ቅጽሮቹን በመጠገንና የቤተ መቅደስዋንም መሠረት በመጣል ላይ ናቸው።
የኤፍራጥስ ምዕራባዊ ክፍል ገዢ የነበረው ታተናይና ሽታርቦዝናይ እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው የሆኑ ለንጉሥ ዳርዮስ የጻፉት ደብዳቤ የሚከተለው ነው፦
እግዚአብሔር ለእስራኤል የሰጣቸውን ሕግና ትእዛዞች ሁሉ የሚያውቅ ሊቅ ለነበረው ለካህኑ ዕዝራ፥ ንጉሠ ነገሥት አርጤክስስ የሰጠው ደብዳቤ ከዚህ የሚከተለው ነው፦
ይህችም ሳምራዊት ሴት ኢየሱስን፦ “አንተ ከአይሁድ ወገን ሆነህ እንዴት እኔን ሳምራዊቷን ‘ውሃ አጠጪኝ!’ ብለህ ትጠይቀኛለህ?” አለችው፤ ይህን ማለትዋ፥ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር ስምምነት ስላልነበራቸው ነው።