ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።
ዕዝራ 2:70 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናቱ፥ ሌዋውያኑና ከሕዝቡም አንዳንዱ በኢየሩሳሌም ወይም በአቅራቢያዋ ሰፈሩ፤ መዘምራኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎችና ለቤተ መቅደሱ ሕንጻ የተመደቡት ሠራተኞች በየአቅራቢያው በሚገኙት ከተሞች ሰፈሩ፤ እንዲሁም የቀሩት እስራኤላውያን የቀድሞ አባቶቻቸው በነበሩባቸው ከተሞች ሰፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ መዘምራኑ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሌሎች ሰዎች ጋራ በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ፤ የቀሩት እስራኤላውያንም በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንዶች፥ መዘምራኑ፥ በር ጠባቂዎቹና፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ፥ በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ ከሕዝቡም አያሌዎች፥ መዘምራኑና በረኞቹም፥ ናታኒምም በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህናቱና ሌዋውያኑ፥ ከሕዝቡም አያሌዎች፥ መዘምራኑና በረኞቹ፥ ናታኒምም በከተሞቻቸው፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ። |
ከዚያም በኋላ ከሶርያውያን ሰፈር በመነሣት ወደ ሰማርያ ተመልሰው ሄዱ፤ እዚያም እንደ ደረሱ የከተማይቱን ቅጽር በር ዘበኞች ጠርተው “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄደን ነበር፤ ነገር ግን ምንም ያየነው ሰው ወይም የሰማነው ድምፅ እንኳ የለም፤ ፈረሶችና አህዮች እንደ ታሰሩ ናቸው፤ ድንኳኖቹም ሶርያውያን ትተዋቸው ስለ ሄዱ ባዶአቸውን ናቸው” ሲሉ ነገሩአቸው።
ባለፉት ዘመናት ሳኦል ንጉሥ ሆኖ ሳለ እንኳ የእስራኤልን ሕዝብ ወደ ጦርነት የምትመራ አንተ ነበርክ፤ ‘ሕዝቤን እስራኤልን የምትመራና የምታስተዳድር አንተ ነህ’ ብሎ አምላክህ እግዚአብሔር ነግሮሃል።”
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ማርኮ ወደ ባቢሎን ከወሰዳቸው ሰዎች መካከል ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደየከተማቸውም የተመለሱት እነዚህ ናቸው።
ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎቹ፥ መዘምራኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንድ ሰዎች የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ በአጠቃላይ እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው ሰፈሩ።