ዕዝራ 10:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኢሜር ጐሣ፦ ሐናኒና ዘባድያ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኢሜር ዘሮች፤ አናኒና ዝባድያ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኢሜርም ልጆች፥ ሐናኒና ዝባድያ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኢሚር ልጆችም አናኒና ዝብድያ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኢሜር ልጆችም፤ አናኒና ዝባድያ። |
ከዚህ የሚከተለው ደግሞ ከምርኮ የተመለሱ የካህናት ቤተሰብ ዝርዝር ነው፦ የኢያሱ ዘር የሆነው የይዳዕያ ቤተሰብ 973 የኢሜር ቤተሰብ 1052 የፓሽሑር ቤተሰብ 1247 የሓሪም ቤተሰብ 1017
የኢዮጼዴቅ ልጅ ኢያሱም ከወገኖቹ ካህናትና የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልም ከዘመዶቹ ጋር በመተባበር የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንደገና ሠሩ፤ የእግዚአብሔር ሰው ለሆነው ለሙሴ በተሰጠው የሕግ መጽሐፍ በተጻፈውም መመሪያ መሠረት በዚያ መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ለማቅረብ ቻሉ።