La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕዝራ 10:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከምርኮ የተመለሱት ሁሉ ይህንኑ ዕቅድ ለመቀበል ተስማሙ፤ ስለዚህም ካህኑ ዕዝራ ከጐሣ መሪዎች መካከል መርጦ አስፈጻሚዎችን በመሾም ስም ዝርዝራቸውን መዝግቦ አኖረ፤ እነርሱም ዐሥረኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን ጉዳዩን መመርመር ጀመሩ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ምርኮኞቹ እንደ ተባለው አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም ከእያንዳንዱ የቤተ ሰብ ምድብ አንዳንድ የቤተ ሰብ ኀላፊ የሆነ ሰው መረጠ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዘገቡ። ከዚያም በዐሥረኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጕዳዩን ለመመርመር ተቀመጡ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ምርኮኞቹም እንዲህ አደረጉ፥ ካህኑ ዕዝራ፥ የአባቶችን መሪዎች መረጠ፤ በየአባቶቻቸው ቤቶች ተለዩ፥ ሁሉም በየስማቸው ተጻፉ፥ በአሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ሊመረምሩ ተቀመጡ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የስ​ደ​ተ​ኞ​ቹም ልጆች እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ ካህኑ ዕዝራ፥ የአ​ባ​ቶ​ችም ቤቶች አለ​ቆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች ሁሉም በየ​ስ​ማ​ቸው ተለዩ፤ በዐ​ሥ​ረ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ነገ​ሩን ይመ​ረ​ምሩ ዘንድ ተቀ​መጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ምርኮኞቹም እንዲህ አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም የአባቶችም ቤቶች አለቆች በየአባቶቻቸው ቤቶች ተለዩ፤ ሁሉም በየስማቸው ተጻፉ፤ በአሥረኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ነገሩን ይመረምሩ ዘንድ ተቀመጡ።

Ver Capítulo



ዕዝራ 10:16
6 Referencias Cruzadas  

ይህም በተነገረ ጊዜ መሹላምና ሻበታይ ተብሎ የሚጠራው አንድ ሌዋዊ ድጋፍ ከሰጡአቸው ከዐሣሔል ልጅ ዮናታንና የቲቅዋ ልጅ ከሆነው ከያሕዘያ በቀር ሌላ ተቃዋሚ አልነበረም።


በሚቀጥለው ዓመት በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ከባዕዳን ሴቶች ጋር የተጋቡትን ሰዎች ጉዳይ በሙሉ መርምረው ጨረሱ።


ለድኾች አባት፥ ለማላውቃቸውም ሰዎች ጠበቃ ነበርኩ።


“በሕጋችን መሠረት አንድ ሰው የክስ መልስ አስቀድሞ ሳይሰማለትና ምን እንዳደረገ ሳይታወቅ ይፈረድበታልን?” አላቸው።


ይህን በምትሰማበት ጊዜ ስለ ጉዳዩ ጠይቀህ ጠለቅ አድርገህ መርምር፤ ይህ አስከፊ የሆነው ጉዳይ በመካከላችሁ መደረጉ በእውነት ከተረጋገጠ፥


በዚያች ከተማ የሚኖሩትን ሰዎች ከከብቶቻቸው ሁሉ ጋር በሙሉ ግደል፤ ያቺንም ከተማ በፍጹም ደምስስ።