ዘፀአት 9:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ግን ዝናቡ፥ በረዶውና ነጐድጓዱ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ እርሱና መኳንንቱ ልባቸውን በማደንደን እንደገና ኃጢአት ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም ዝናቡ፣ በረዶውና ነጐድጓዱ መቆሙን ባየ ጊዜ እንደ ገና በደለ፤ እርሱና ሹማምቱ ልባቸውን አደነደኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ዝናቡ፥ በረዶውና ነጎድጓዱ እንደ ቆመ ባየ ጊዜ ኃጢአትን ጨመረ፥ እርሱና አገልጋዮቹም ልባቸውን አደነደኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ዝናቡ፥ በረዶውም፥ ነጐድጓዱም ጸጥ እንደ አለ በአየ ጊዜ በደልን ጨመረ፤ እርሱና ሹሞቹም ልባቸውን አደነደኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ዝናቡ በረዶውም ነጎድጓዱም እንደ ተቍረጠ ባየ ጊዜ ኃጢያትን ጨመረ፤ እርሱና ባሪያዎቹም ልባቸውን አደነደኑ። |
አባቱ እንዳደረገው ሁሉ ራሱን በትሕትና ዝቅ አድርጎ በማዋረድ ወደ እግዚአብሔር አልተመለሰም፤ እንዲያውም ከአባቱ ይበልጥ የከፋ ኃጢአት ሠራ።
ሴዴቅያስ፥ ታማኝ እንዲሆንለት በእግዚአብሔር ስም ባስማለው በንጉሥ ናቡከደነፆር ላይ ዐመፀ፤ ተጸጽቶ ንስሓ በመግባት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ በእልኸኛነት እምቢ አለ።
እንደገናም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ አሁን ወደ ግብጽ መመለስህ ስለ ሆነ፥ በሰጠሁህ ኀይል የምታደርጋቸውን ተአምራት በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ፤ ሆኖም እኔ የፈርዖንን ልብ ስለማደነድን ሕዝቡን በቀላሉ አይለቅም።
ሰዎች ሆን ብለው ወንጀል የሚሠሩት ለምንድን ነው? የዚህ ምክንያት ሌላ ሳይሆን ወንጀል በሚሠሩ ሰዎች ላይ ፈጣን የቅጣት ፍርድ ባለመሰጠቱ ነው።
የግብጽ ንጉሥና ግብጻውያን እንዳደረጉት ስለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ? እስራኤላውያን የግብጽን ምድር ለቀው የወጡት፥ እግዚአብሔር ግብጻውያንን በብርቱ ከቀጣቸው በኋላ አልነበረምን?