ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በነገው ቀን ዝንቦቹ ከአንተና ከመኳንንቱ ከሕዝቡም ዘንድ እንዲወገዱ ከአንተ እንደ ተለየሁ አሁኑኑ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ እንዳይሄዱ በመከልከል እንደገና ልታሞኘኝ አይገባም።”
ዘፀአት 9:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን አንተና መኳንንትህ ገና እግዚአብሔር አምላክን የማትፈሩ መሆናችሁን ዐውቃለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም አንተና ሹማምትህ አሁንም ቢሆን እግዚአብሔር አምላክን እንደማትፈሩ ዐውቃለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተና አገልጋዮችህ ጌታ አምላክን ገና እንደማትፈሩ አውቃለሁና።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን አንተና ሹሞችህ እግዚአብሔር አምላክን ምንጊዜም እንደማትፈሩ አውቃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን አንተና ባሪያዎችህ አምላክን እግዚአብሔርን ገና እንደማትፈሩ አውቃለሁ፤” አለው። |
ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “በነገው ቀን ዝንቦቹ ከአንተና ከመኳንንቱ ከሕዝቡም ዘንድ እንዲወገዱ ከአንተ እንደ ተለየሁ አሁኑኑ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ይሠዉ ዘንድ እንዳይሄዱ በመከልከል እንደገና ልታሞኘኝ አይገባም።”
ክፉ ሰዎች ቸርነት ብታደርግላቸው እንኳ መልካም መሥራትን አይማሩም፤ በዚህ ጽድቅ በሰፈነበት ምድር እያሉ እንኳ ክፋት ከማድረግ አይቈጠቡም፤ ታላቅነትህንም አይገነዘቡም።
አምላክ ሆይ! ለምን መንገድህን እንድንስት አደረግኸን? እንዳንፈራህስ ለምን ልባችንን አደነደንክ? ለአገልጋዮችህ፥ የአንተ ስለ ሆኑት ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።