La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፀአት 40:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የተቀደሱትን ልብሶች አልብሰህ በመቀባት አሮንን ለእኔ የተለየ ካህን ሆኖ እንዲያገለግለኝ አድርገው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም አሮንን የተቀደሰውን ልብስ አልብሰው፤ ካህን ሆኖ ያገለግለኝ ዘንድ ቅባው፤ ቀድሰውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሮንን የተቀደሰውን ልብስ ታለብሰዋለህ፥ ካህን እንዲሆነኝ ትቀባዋለህ፥ ትቀድሰውማለህ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለአ​ሮ​ንም የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ልብስ ታለ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ ካህ​ንም ይሆ​ነ​ኛል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የተቀደሰውንም ልብስ አሮንን ታለብሰዋለህ፤ በክህነትም ያገለግለኝ ዘንድ ቀብተህ ትቀድሰዋለህ።

Ver Capítulo



ዘፀአት 40:13
13 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ እነዚህን ልብሶች ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ አልብሳቸው፤ በክህነት ያገለግሉኝም ዘንድ የወይራ ዘይት በመቀባት የክህነትን ማዕርግ ትሰጣቸዋለህ፤ ትቀድሳቸዋለህም፤


የቅባት ዘይቱንም ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ቀባው፤


ልጆቹንም አምጥተህ ቀሚስ አልብሳቸው።


ለተጨቈኑት መልካም ዜናን አበሥር ዘንድ፥ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩት ነጻነትን፥ ለታሰሩት መፈታትን ለማወጅ እግዚአብሔር ቀብቶ ስለ ላከኝ፥ የጌታ እግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው።


ይህም እግዚአብሔር አሮንንና ልጆቹን ካህናት አድርጎ በሾመበት ቀን ለእግዚአብሔር ከቀረበው ከሚቃጠል መሥዋዕት ለካህናት ድርሻ ሆኖ የተለየ ነው፤


በዚያን ቀን እግዚአብሔር ይህን የመሥዋዕት ክፍል ለካህናቱ እንዲሰጡአቸው የእስራኤልን ሕዝብ አዘዘ፤ ይህም በሚመጡት ዘመናት ሁሉ የካህናቱ ድርሻ እንዲሆን ቋሚ ሥርዓት አደረገው።”


ቀጥሎም ሙሴ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት የአሮንን ወንዶች ልጆች ወደፊት አቅርቦ ቀሚስ አለበሳቸው፤ በወገባቸውም ዙሪያ መታጠቂያ አድርጎ በራሳቸውም ላይ ቆብ ደፋላቸው።


እነርሱ በእውነት ቅዱሳን እንዲሆኑ እኔ ራሴን ስለ እነርሱ ቅዱስ አደርጋለሁ።


እግዚአብሔር መንፈሱን የሚሰጠው መጥኖ ስላልሆነ እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራል።


በዚህም “ፈቃድ” በሚለው ቃል መሠረት ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ አንዴ በማያዳግም ሁኔታ መሥዋዕት ሆኖ በመቅረቡ ምክንያት ተቀድሰናል።


ታዲያ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፥ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳን ደም ያረከሰ፥ የጸጋን መንፈስ የሰደበ፥ እንዴት ያለ የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል!


እናንተ ግን ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ቀብቶአችኋል። ስለዚህ ሁላችሁም ሁሉን ነገር ታውቃላችሁ።


ከክርስቶስ የተቀበላችሁት መንፈስ በውስጣችሁ ስለሚኖር ሌላ አስተማሪ አያስፈልጋችሁም፤ እርሱ ሁሉን ነገር ያስተምራችኋል፤ የሚያስተምራችሁም እውነትን ነው እንጂ ሐሰትን አይደለም። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንዳስተማራችሁ በክርስቶስ ኑሩ።