ዘፀአት 39:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከወርቅ ክር፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና፥ ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ በብልኀት የተጠለፈው ቀበቶ አንድ ወጥ በመሆን ከኤፉዱ ጋር ተያይዞ ተሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጥበብ የተፈተለው መታጠቂያ በተመሳሳይ መልክ ሆኖ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው፣ ከኤፉዱ ጋራ አንድ ወጥ የሆነና ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ በቀጭኑ ከተፈተለ ሐር የተሠራ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ ቋድ እንደ እርሱ ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠራ ነበረ፥ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ከእርሱ ጋር ወጥ ሆኖ የተሠራ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እርስዋን ከወርቅ፥ ከሰማያዊና ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃም፥ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም እንደ ሠሩ የልብሰ መትከፉን ቋድ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላዩም መታጠቂያ ሆኖ በብልሃት የተጠለፈው የኤፉዱ ቍድ እንደ እርሱ ከእርሱም ጋር አንድ ነበረ፤ ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ የተሠራ ነበረ። |
ከዚህ በኋላ አሮንን የክህነት ልብስ አልብሰው፤ ሸሚዙን፥ ኤፉዱን፥ የኤፉዱን መደረቢያ ቀሚስ፥ የደረት ኪሱን አልብሰው፤ መታጠቂያውን አስታጥቀው፤
የመረግድ ድንጋዮችንም አዘጋጅተው በወርቅ ፈርጥ ላይ አስቀመጡአቸው፤ በእነርሱም ላይ የዐሥራ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች ስሞች እንደ ቀለበት ማኅተም ተቀርጸውባቸው ነበር፤
አሮንን ቀሚስ አልብሶ፥ ካባ ደርቦ፥ መታጠቂያ አስታጠቀው፤ በዚያም ላይ ኤፉድ አደረገለት፤ እርሱንም በልዩ ጥበብ በተጠለፈ ቀበቶ አያይዞ በወገቡ ዙሪያ አሰረለት፤
በመቅረዞቹ መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፤ እርሱ እስከ እግሩ የሚደርስ ረጅም ልብስ የለበሰ፥ ደረቱን በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበረ።