ዘፀአት 38:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም በሕዝብ ቈጠራ ጊዜ የተመዘገቡት ሰዎች እያንዳንዳቸው በይፋ በታወቀው ሚዛን ልክ የከፈሉትን ድርሻ ጠቅላላ ድምር የሚያኽል ነበር፤ በሕዝብ ቈጠራ የተመዘገቡትም ኻያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያም በላይ የሆኑት ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ ኀምሳ ወንዶች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተቈጠሩት ጋራ ዐብረው ከሆኑት ሃያና ከሃያ ዓመት በላይ የሆናቸው ስድስት መቶ ሦስት ሺሕ ዐምስት መቶ ዐምሳ ሰዎች የሰጡት እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን በአንድ ሰው አንድ ቤካ ይኸውም ግማሽ ሰቅል ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት፥ የሰቅል ግማሽ ከተቆጠረው ከእያንዳንዱ ሰው የተሰጠ ነው፤ ይህም ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያ በላይ የተቆጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እያንዳንዱም ሰው አንድ አንድ ዲድርክም አዋጣ፤ አንድ ዲድርክም እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን የሰቅል ግማሽ ነው፤ ይህም የተዋጣው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ከተቈጠሩ ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን፥ የሰቅል ግማሽ ከተቈጠረው ከእያንዳንዱ ሰው የተሰጠ ነው፤ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የተቈጠሩት ሁሉ ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ሰዎች ነበሩ። |
“የእስራኤልን ሕዝብ በምትቈጥርበት ጊዜ በሕዝብ ቈጠራው ወቅት መቅሠፍት እንዳይደርስባቸው እያንዳንዱ ሰው ለሕይወቱ ቤዛ የሚሆን ዋጋ ይክፈል።
ከሕዝብ ቈጠራ ውስጥ የሚገባ እያንዳንዱ ሰው በተቀደሰው ድንኳን በታወቀው ሚዛን ልክ አንድ ጥሬ ብር ይክፈል፤ እያንዳንዱ ሰው ይህን ለእግዚአብሔር መባ አድርጎ ያቅርብ፤
ከብሩም ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚሆነው ለተቀደሰው ድንኳንና ለመጋረጃዎች መቆሚያ የሚሆኑ አንድ መቶ እግሮች የተሠሩበት ነበር፤ ይኸውም ለእያንዳንዱ እግር ሠላሳ አራት ኪሎ ግራም ተመድቦለት ነው።
“አንተና አሮን፥ የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ በየነገዱና በየቤተሰቡ ኻያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነውን እያንዳንዱን ወንድ አንድ በአንድ እየቈጠራችሁ መዝግቡ።
“በመላው የእስራኤል ማኅበር በየቤተሰቡ ዕድሜአቸው ኻያ ዓመት የሞላቸውንና ከዚያም በላይ የሆኑትን፥ ወታደር ሆነው ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ወንዶች ልጆች ሁሉ ቊጠሩ።”
ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅፍርናሆም በደረሱ ጊዜ የቤተ መቅደስ ግብር ተቀባዮች ወደ ጴጥሮስ ቀረቡና፥ “መምህራችሁ የቤተ መቅደስ ግብር አይከፍልምን?” ሲሉ ጠየቁት።