ዘፀአት 38:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከይሁዳ ነገድ የሑር የልጅ ልጅ የሆነው የኡሪ ልጅ ባጽልኤል፥ እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ሁሉን ነገር ሠራ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከይሁዳ ነገድ የሆር የልጅ ልጅ፣ የኡሪ ልጅ የሆነው ባስልኤል፣ እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከይሁዳ ነገድ የሆነው የሑር ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤል ጌታ ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሁዳ ነገድም የሆነ የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤል እግዚአብሔር ለሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ አደረገ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከይሁዳ ነገድም የሆነ የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤል እግዚአብሔር ለሙሴ ያዘዘውን ሁሉ አደረገ። |
እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፦ “ ‘ገና ልጅ ነኝ’ አትበል፤ የምትሄደው እኔ ወደምልክህ ቦታ ነው፤ የምትናገረውም እኔ የማዝህን ሁሉ ነው፤