Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 38:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሒሳማክ ልጅ አሆሊአብም አንጥረኛ፥ ፕላን አውጪ ባለሞያ፥ እንዲሁም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ እየጠለፈ ጥሩ በፍታ የሚሠራ ሸማኔ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ከርሱም ጋራ ከዳን ነገድ የሆነው የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ፣ ዕቅድ አውጭና የእጅ ጥበብ ባለሙያ፣ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በቀጭን በፍታ ጥልፍ ጠላፊ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነው የአሒሳማክ ልጅ ኤልያብ ነበረ፤ እርሱም ቀራጭ፥ ንድፍ አውጪ፥ እንዲሁም በሰማያዊ በሐምራዊ፥ በቀይ ግምጃና በጥሩ በፍታ የሚጠልፍ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ከእ​ር​ሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነ የአ​ሒ​ሳ​ሚክ ልጅ ኤል​ያብ ነበረ፤ እር​ሱም በሰ​ማ​ያዊ፥ በሐ​ም​ራዊ፥ በቀ​ይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍታ የሽ​መና ሥራ ይሠራ ዘንድ የቅ​ርጽ፥ የሽ​መ​ናና የጥ​ልፍ ሥራ አለቃ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ከእርሱም ጋር ከዳን ነገድ የሆነ የአሂሳሚክ ልጅ ኤልያብ ነበረ፤ እርሱም የቅርጽ ሠራተኛና ብልህ ሠራተኛ፥ በሰማያዊ በሐምራዊም በቀይም ግምጃ፥ በጥሩም በፍታ የሚሠራ ጠላፊ ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 38:23
6 Referencias Cruzadas  

ሰማያዊና ሐምራዊ፥ ቀይም ከፈይ፥ ጥሩ በፍታ፥ ከፍየል ጠጒር የተሠራ ልብስ፥


“ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ በጥልፍ ያጌጠ መጋረጃ አድርግለት።


“እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሑር የልጅ ልጅ የሆነውን የኡሪን ልጅ ባጽልኤልን በስም ጠርቼአለሁ።


ከእርሱም ጋር እንዲሠራ ከዳን ነገድ የአሒሳማክን ልጅ ኦሆሊአብን መርጬአለሁ፤ እኔ ያዘዝኩህን ነገር ሁሉ እንዲሠሩ ሌሎችም የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎች ሁሉ ታላቅ ችሎታ እንዲኖራቸው አድርጌአለሁ።


ለእርሱና ከዳን ወገን የአሒሳማክ ልጅ ለሆነው ኦሆሊአብ የእጅ ጥበብ ዕውቀታቸውን ለሌሎች የማስተማርን ችሎታ ሰጥቶአቸዋል።


“ባጽልኤልና ኦሆሊአብ እንዲሁም ለተቀደሰው ድንኳን ዝግጅት እግዚአብሔር ማናቸውንም ሥራ ለመሥራት ችሎታንና ዕውቀትን የሰጣቸው ሌሎች ሰዎች እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ይሠራሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos