እነርሱ እንዲከተሉት ካዘዝኳቸው መንገድ ወዲያውኑ ወጥተዋል፤ ከቀለጠ ወርቅ ጥጃ ሠርተውም ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለት ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን አምላካችን ይህ ነው’ ብለዋል።
ዘፀአት 32:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ‘ያ ከግብጽ መርቶ ያወጣን ሰው፥ ሙሴ ምን እንደ ደረሰበት አናውቅም፤ ስለዚህ በፊታችን እየሄዱ የሚመሩን አማልክት ሥራልን’ አሉኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ‘በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን፤ ያ ከግብጽ ያወጣን ሙሴ ምን እንዳገኘው አናውቅም’ አሉኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ ‘ይህ ከግብጽ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ደረሰበት አናውቅምና በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን’ አሉኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን አሉኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ ይህ ከግብፅ ምድር ያወጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አናውቅምና በፊታችን የሚሄዱ አማልክት ሥራልን አሉኝ። |
እነርሱ እንዲከተሉት ካዘዝኳቸው መንገድ ወዲያውኑ ወጥተዋል፤ ከቀለጠ ወርቅ ጥጃ ሠርተውም ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለት ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን አምላካችን ይህ ነው’ ብለዋል።
ሳኦልም “እነርሱ ወታደሮቼ ከዐማሌቃውያን የማረኩአቸው ናቸው፤ ምርጥ ምርጥ የሆኑትን የቀንድ ከብቶችና በጎች ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ለማቅረብ አምጥተዋል፤ የቀሩትን ግን በሙሉ ደምስሰናል” ሲል መለሰለት።
ነገር ግን ወታደሮቼ የማረኩአቸውን ምርጥ ምርጥ የሆኑ በጎችንና የቀንድ ከብቶችን አልገደሉአቸውም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ በጌልገላ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አድርገው ለማቅረብ አምጥተዋቸዋል።”