ዘፀአት 3:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በምትወጡበት ጊዜ ሕዝቡ በግብጻውያን ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙ ስለማደርግ ባዶ እጃችሁን አትወጡም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህ ሕዝብ በግብጻውያን ዘንድ የመወደድን ጸጋ እንዲያገኝ ስለማደርግ በምትወጡበት ጊዜ ባዶ እጃችሁን አትሄዱም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግብፃውያንም ፊት ለዚህ ሕዝብ ሞገስን እሰጣለሁ፤ እንዲህም ይሆናል፥ በሄዳችሁ ጊዜ ባዶ እጃችሁን አትሄዱም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግብፃውያንም ፊት ለዚህ ሕዝብ ሞገስን እሰጣለሁ፤ በምትሄዱም ጊዜ ባዶ እጃችሁን አትሄዱም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብፃውያንም ፊት ለዚህ ሕዝብ ሞገስን እሰጣለሁ፤ እንዲህም ይሆናል፤ በሄዳችሁ ጊዜ ባዶ እጃችሁን አትሄዱም፤ |
እነሆ፥ አሁንም የእኔን ጸሎት ስማ፤ አንተን ማክበር የሚወዱትን የሌሎችንም አገልጋዮችህን ጸሎት አድምጥ፤ ዛሬ ልሠራው ያቀድኩት ይሳካልኝ ዘንድ የንጉሠ ነገሥቱን ልብ በማራራት እርዳኝ።” እነሆ፥ እኔ በዚህ ጊዜ የንጉሠ ነገሥቱ ወይን ጠጅ አሳላፊ ነበርኩ።
እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በግብጻውያን ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙ አደረገ፤ በእርግጥም የንጉሡ ባለሟሎችና ሕዝቡ ሁሉ ሙሴን በግብጽ ምድር ታላቅ ሰው አድርገው ተመለከቱት።
እግዚአብሔርም እስራኤላውያን በግብጻውያን ዘንድ ሞገስ እንዲያገኙና የጠየቁትንም ሁሉ ማግኘት እንዲችሉ አደረገ፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን የግብጽን ሀብት በዝብዘው ሄዱ።