ዘፀአት 23:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የጠላትህ በሬ ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኝ መልስለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የጠላትህ በሬ ወይም አህያ ሲባዝን ብታገኘው ወደ እርሱ መልሰው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጠላትህን በሬ ወይም አህያ ጠፍቶ ብታገኘው ለእርሱ መልስለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የጠላትህን በሬ ወይም አህያውን ጠፍቶ ብታገኘው ፈጽሞ መልስለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጠላትህን በሬ ወይም አህያውን ጠፍቶ ብታገኘው በፍጹም መልስለት። |
እኔ ግን ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁን መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁ በጎ አድርጉ፤ ክፉ ለሚያደርጉባችሁና ለሚያሳድዱአችሁ ጸልዩ” እላችኋለሁ።
ማንም ሰው በክፉ ፋንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ይልቅስ ሁልጊዜ እናንተ ለእርስ በርሳችሁም ሆነ እንዲሁም ለሌሎች ሰዎች ሁሉ መልካም ለማድረግ ትጉ።