ዘፀአት 22:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው እንስሶቹ በመስክ ወይም በወይን ተክል ቦታ አሰማርቶ ሳለ እንስሶቹ ወደ ሌላ ሰው እርሻ ገብተው ሰብሉን ቢበሉት ከራሱ ማሳ ወይም የወይን ተክል ቦታ ከሚያገኘው ምርት ካሣ ይክፈል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው ከብቶቹን በመስክ ወይም በወይን ቦታ አሰማርቶ እንዲሁ ስድ ቢለቅቃቸውና የሌላውን ሰው መስክ ቢግጡ፣ ምርጥ ከሆነው ከራሱ መስክ ወይም የወይን ቦታ መክፈል አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሳት ቢነሣ፥ እሾኽንም ቢይዝ፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል ወይም እርሻውን ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያነደደው ይካስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የሰውን አዝመራ ከብቱን ያስበላ፥ የሌላ ሰው ወይንንም ያስበላ ሰው ቢኖር ግምቱን ይክፈል። የሰውን አዝመራ ፈጽሞ ቢያስበላ ግን በአጠገቡ ባለ አዝመራ ልክ ይክፈል፤ ወይንም ቢሆን በአጠገቡ ባለ ወይን ልክ ይክፈል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም ሰው ወደ እርሻ ወይም ወደ ወይን ስፍራ ከብቱን ቢነዳው፥ የሌላውንም እርሻ ቢያስበላ፥ ከተመረጠ እርሻው ከማለፊያውም ወይኑ ይካስ። |
“አንድ ሰው በእርሻው ውስጥ እሳት ቢያቀጣጥልና እሳቱ በቊጥቋጦ ተላልፎ ወደ ሌላው ሰው እርሻ በመዛመት በማደግ ላይ ያለውንም ሆነ ታጭዶ የተከመረውን እህል ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይክፈል።
ለም ወደሆነችው ምድር እንዳላመጣኸን ወይም የእርሻና የወይን ተክል ቦታ እንዳላወረስከን የተረጋገጠ ነው፤ አሁን ደግሞ ልታታልለን ትፈልጋለህ፤ እንግዲህስ ወደ አንተ አንመጣም!”