Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 22:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እሳት ቢነሣ፥ እሾኽንም ቢይዝ፥ ክምሩንም ወይም ያልታጨደውን እህል ወይም እርሻውን ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያነደደው ይካስ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 “አንድ ሰው ከብቶቹን በመስክ ወይም በወይን ቦታ አሰማርቶ እንዲሁ ስድ ቢለቅቃቸውና የሌላውን ሰው መስክ ቢግጡ፣ ምርጥ ከሆነው ከራሱ መስክ ወይም የወይን ቦታ መክፈል አለበት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “አንድ ሰው እንስሶቹ በመስክ ወይም በወይን ተክል ቦታ አሰማርቶ ሳለ እንስሶቹ ወደ ሌላ ሰው እርሻ ገብተው ሰብሉን ቢበሉት ከራሱ ማሳ ወይም የወይን ተክል ቦታ ከሚያገኘው ምርት ካሣ ይክፈል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “የሰ​ውን አዝ​መራ ከብ​ቱን ያስ​በላ፥ የሌላ ሰው ወይ​ን​ንም ያስ​በላ ሰው ቢኖር ግም​ቱን ይክ​ፈል። የሰ​ውን አዝ​መራ ፈጽሞ ቢያ​ስ​በላ ግን በአ​ጠ​ገቡ ባለ አዝ​መራ ልክ ይክ​ፈል፤ ወይ​ንም ቢሆን በአ​ጠ​ገቡ ባለ ወይን ልክ ይክ​ፈል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ማንም ሰው ወደ እርሻ ወይም ወደ ወይን ስፍራ ከብቱን ቢነዳው፥ የሌላውንም እርሻ ቢያስበላ፥ ከተመረጠ እርሻው ከማለፊያውም ወይኑ ይካስ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 22:5
7 Referencias Cruzadas  

የድካሙን ፍሬ ሳይውጠው ይመልሰዋል፥ እንደ ንግዱም ትርፍ አይደሰትም።


የጉድጓዱ ባለቤት ዋጋውን ለባለቤቱ ይክፈል፤ የሞተውም ለእርሱ ይሁን።


በአውሬ ተበልቶ ከሆነ የቀረውን ለምስክርነት ያምጣው፤ በአውሬም ስለተበላ አይክፈል።


የሰረቀው በሬ ወይም አህያ ወይም በግ ቢሆንና በሕይወት ሳለ በእጁ ቢገኝ፥ የሰረቀውን ሁለት እጥፍ አድርጎ ይክፈል።


አንድ ሰው በእርሻ ወይም በወይን ስፍራ ከብቱን ቢያሰማራ፥ የሌላውንም ሰው እርሻ ቢያስበላ፥ ከተመረጠ እርሻውና መልካም ከሆንው ወይኑ ይካስ።


አንድ ሰው ብር ወይም ሌላ ነገር እንዲጠብቅለት ለባልንጀራው በአደራ ቢሰጥ፥ ከቤቱም ቢሰረቅና ሌባው ቢገኝ እጥፍ ይክፈል።


ደግሞስ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር አላስገባኸንም፥ እርሻና የወይንም ተክል ቦታ አላወረስከንም፤ የእነዚህንስ ሰዎች ዐይኖቻቸውን ታወጣለህን? አንመጣም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos