ዘፀአት 21:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእንስሳውን ዋጋ ይክፈል፤ ገንዘቡን ለእንስሳው ባለቤት ከከፈለ በኋላ የሞተውን እንስሳ ለራሱ ያስቀር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጕድጓዱ ባለቤት ኪሳራ ይክፈል፤ ለባለቤቱ መክፈል አለበት፤ የሞተውም እንስሳ ለርሱ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጉድጓዱ ባለቤት ዋጋውን ለባለቤቱ ይክፈል፤ የሞተውም ለእርሱ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጕድጓዱ ባለቤት ዋጋቸውን ለባለቤታቸው ይክፈል፤ የሞተውም ለእርሱ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጕድጓዱ ባለቤት ዋጋቸውን ለባለቤታቸው ይክፈል፤ የሞተውም ለእርሱ ይሁን። |
የአንድ ሰው በሬ የሌላውን ሰው በሬ ወግቶ ቢገድል ሁለቱ ሰዎች በሕይወት ያለውን በሬ ሸጠው ገንዘቡን ለሁለት ይካፈሉት፤ የሞተውንም በሬ ሥጋ ለሁለት ይካፈሉ።
“አንድ ሰው በእርሻው ውስጥ እሳት ቢያቀጣጥልና እሳቱ በቊጥቋጦ ተላልፎ ወደ ሌላው ሰው እርሻ በመዛመት በማደግ ላይ ያለውንም ሆነ ታጭዶ የተከመረውን እህል ቢያቃጥል፥ እሳቱን ያቀጣጠለው ሰው ካሣ ይክፈል።
ይህም ማለት፥ ስለ ብድር በመያዣ ስም የያዘውን ወይም የሰረቀውን ንብረት ቢመልስ፥ ኃጢአት መሥራትን ትቶ ሕይወትን የሚሰጡ ሕጎችን ቢጠብቅ፥ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም፤