ያዕቆብ ያጐቱን የላባን በጎች እየነዳች ስትመጣ ራሔልን አይቶ ወደ ጒድጓዱ ሄደ፤ ጒድጓዱ የተከደነበትንም ድንጋይ አንከባሎ በጎቹን አጠጣቸው።
ዘፀአት 2:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “አንድ ግብጻዊ ከእረኞች እጅ አዳነን፤ እንዲያውም ውሃ እየቀዳ መንጋችንን አጠጣልን” ብለው መለሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “አንድ ግብጻዊ ከእረኞች እጅ አዳነን፤ እንዲያውም ውሃ ቀድቶ በጎቻችንን አጠጣልን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም፦ “አንድ ግብፃዊ ሰው ከእረኞች እጅ አዳነን፥ ደግሞም ቀዳልን፥ በጎቻችንንም አጠጣ” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “አንድ የግብፅ ሰው ከእረኞች እጅ አዳነን፤ ደግሞም ቀዳልን፤ በጎቻችንንም አጠጣልን” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ “አንድ የግብፅ ሰው ከእረኞች እጅ አዳነን፤ ደግሞም ቀዳልን፤ በጎቻችንንም አጠጣ፤” አሉ። |
ያዕቆብ ያጐቱን የላባን በጎች እየነዳች ስትመጣ ራሔልን አይቶ ወደ ጒድጓዱ ሄደ፤ ጒድጓዱ የተከደነበትንም ድንጋይ አንከባሎ በጎቹን አጠጣቸው።
በዚያ የሚኖሩ ከነዓናውያን በአጣድ አውድማ ለቅሶውን ባዩ ጊዜ “ይህ የግብጻውያን ለቅሶ እንዴት መሪር ነው?” አሉ። በዚህ ምክንያት በዮርዳኖስ ሜዳ ያለው የዚያ ቦታ ስም “አቤል ምጽራይም” ተባለ፤ ትርጒሙም በዕብራይስጥ “የግብጻውያን ለቅሶ” ማለት ነው።