ዘፀአት 17:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም አለ “የእግዚአብሔርን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጋችሁ ያዙ! እግዚአብሔር ዐማሌቃውያንን ለዘለዓለም ይዋጋቸዋል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እጆች ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተዘርግተዋልና፤ እግዚአብሔር አማሌቃውያንን ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዋጋቸዋል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “እጅ በጌታ ዙፋን ላይ ስለጫነ የጌታ ሰልፍ በአማሌቅ ላይ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይሁን አለ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በተሰወረች እጅ ዐማሌቅን እስከ ልጅ ልጅ ይዋጋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ እጁን በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ስለጫነ የእግዚአብሔር ሰልፍ በአማሌቅ ላይ ለልጅ ልጅ ይሁን አለ። |
እግዚአብሔር በመዝሙር የማመሰግነው መከላከያ ኀይሌ ነው፤ ከጠላት እጅ ያዳነኝ ታዳጊዬም እርሱ ነው፤ እርሱ አምላኬ ስለ ሆነ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴም አምላክ ስለ ሆነ፥ ስለ ገናናነቱ እዘምራለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ለእኔ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበትስ ቦታ ምን ዐይነት ነው?
‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ ማሳረፊያ ናት፤ ታዲያ ለእኔ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበትስ ቦታ ምን ዐይነት ነው? ይላል ጌታ።