ዘፀአት 15:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቊጣህ እስትንፋስ፥ ውሃው ወደ ላይ ተቈለለ፤ እንደ ግድግዳም ቀጥ ብሎ ቆመ፤ በጥልቅ ስፍራ ያለውም ውሃ፥ ረግቶ ጠጠረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአፍንጫህ እስትንፋስ፣ ውሆች ተቈለሉ፤ ፈሳሾችም እንደ ግድግዳ ቆሙ፤ የጥልቁ ውሃ ባሕሩ ውስጥ ረጋ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአፍንጫህ እስትንፋስ ውኆች ተከመሩ፥ ፈሳሾቹም እንደ ክምር ቆሙ፤ ጥልቁም በባሕር ልብ ውስጥ ረጋ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቍጣህ እስትንፋስ ውኃው ቆመ፤ ውኃዎች እንደ ግደግዳ ቆሙ፤ ሞገዱም በባሕር መካከል ረጋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአፍንጫህ እስትንፋስ ውኆች ተከመሩ፤ ፈሳሾቹም እንደ ክምር ቆሙ፤ ሞገዱም በባሕር ውስጥ ረጋ። |
ነገር ግን በእውነት ለድኾች ይፈርዳል፤ ረዳት ለሌላቸውም ወገኖች ተከላካይ በመሆን መብታቸውን ያስከብራል፤ በበትር እንደሚመታ፥ መረን በተለቀቁት ላይ ይፈርዳል፤ በቃሉም ክፉዎችን ያጠፋል።
ተራራዎች አንተን አይተው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ የዝናብም ጐርፍ ምድርን እየጠራረገ አለፈ፤ ውቅያኖስ ከፍተኛ ድምፅ አሰማ፤ ማዕበሉም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ።
የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች ውሃውን በሚነኩበት ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ ውሃ መውረዱን ያቆማል፤ ከላይ እየጐረፈ የሚመጣውም ውሃ በአንድ ቦታ ተሰብስቦ ይቈለላል።”
ውሃው መውረዱን አቆመ፤ በጻርታን አጠገብ አዳም ተብላ እስከምትጠራው ከተማ ድረስ ተከመረ፤ ወደ ሙት ባሕር ይፈስ የነበረውም ጐርፍ በፍጹም ተቋረጠ፤ ስለዚህም ሕዝቡ ወደ ማዶ ወደ ኢያሪኮ ተሻገሩ።