ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ አለቆች ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ቤተሰባችሁ ሁሉ የፋሲካን በዓል እንዲያከብር ከእናንተ እያንዳንዱ ጠቦት መርጦ ይረድ፤
ዘፀአት 13:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአህያ የተወለደውን በኲር ግን የበግ ጠቦት በመተካት ከእግዚአብሔር እጅ ትዋጁታላችሁ፤ አህያውን ለመዋጀት ካልፈለጋችሁ ግን አንገቱን ስበሩት፤ በኲር የሆነውንም ወንድ ልጅ ሁሉ መዋጀት ይገባችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአህያ በመጀመሪያ የተወለደውን ውርንጫ ግን በጠቦት ትዋጁታላችሁ፤ አህያውን ካልዋጃችሁት ግን ዐንገቱን ስበሩት። ከወንድ ልጆቻችሁ መካከል በኵር የሆኑትን ሁሉ ዋጁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአህያውን በኩር በጠቦት ትዋጀዋለህ፥ ባትዋጀውም አንገቱን ትሰብረዋለህ፤ የሰውንም በኩር ሁሉ ከልጆችህ መካከል ትዋጀዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአህያውን በኵር በበግ ትለውጠዋለህ፤ ባትለውጠው ግን ትዋጀዋለህ። የሰውንም በኵር ሁሉ ከልጆችህ መካከል ትዋጀዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአህያውን በኵር በጠቦት ትዋጀዋለህ፤ ባትዋጀውም አንገቱን ትሰብረዋለህ፤ የሰውንም በኵር ሁሉ ከልጆችህ መካከል ትዋጀዋለህ። |
ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ አለቆች ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፤ “ቤተሰባችሁ ሁሉ የፋሲካን በዓል እንዲያከብር ከእናንተ እያንዳንዱ ጠቦት መርጦ ይረድ፤
“ከእስራኤል ሕዝብም ሆነ ከእንስሶቹ በኲር ሆኖ የተወለደ ሁሉ ለእኔ መሆን ይገባዋል፤ ስለዚህ በኲር ሆኖ የተወለደውን ሁሉ ለእኔ እንዲሆን ቀድሰው።”
ነገር ግን የበግ ጠቦት በመተካት የአህያን በኲር ለመዋጀት ትችላላችሁ፤ የማትዋጁት ከሆነ ግን አንገቱን ቈልምሙት፤ በኲር ሆኖ የተወለደውንም ወንድ ልጅ ሁሉ ትዋጃላችሁ። “መባ ሳይዝ ማንም ሰው ባዶ እጁን በፊቴ አይታይ።
እነርሱ ድንግሎች ስለ ሆኑ ከሴቶች ጋር ግንኙነት በማድረግ አልረከሱም፤ በጉ ወደሚሄድበትም ሁሉ ይከተሉታል። እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለበጉ ከሰዎች መካከል እንደ በኲራት የቀረቡ ናቸው።