Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 13:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 የአ​ህ​ያ​ውን በኵር በበግ ትለ​ው​ጠ​ዋ​ለህ፤ ባት​ለ​ው​ጠው ግን ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ። የሰ​ው​ንም በኵር ሁሉ ከል​ጆ​ችህ መካ​ከል ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ከአህያ በመጀመሪያ የተወለደውን ውርንጫ ግን በጠቦት ትዋጁታላችሁ፤ አህያውን ካልዋጃችሁት ግን ዐንገቱን ስበሩት። ከወንድ ልጆቻችሁ መካከል በኵር የሆኑትን ሁሉ ዋጁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 የአህያውን በኩር በጠቦት ትዋጀዋለህ፥ ባትዋጀውም አንገቱን ትሰብረዋለህ፤ የሰውንም በኩር ሁሉ ከልጆችህ መካከል ትዋጀዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ከአህያ የተወለደውን በኲር ግን የበግ ጠቦት በመተካት ከእግዚአብሔር እጅ ትዋጁታላችሁ፤ አህያውን ለመዋጀት ካልፈለጋችሁ ግን አንገቱን ስበሩት፤ በኲር የሆነውንም ወንድ ልጅ ሁሉ መዋጀት ይገባችኋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 የአህያውን በኵር በጠቦት ትዋጀዋለህ፤ ባትዋጀውም አንገቱን ትሰብረዋለህ፤ የሰውንም በኵር ሁሉ ከልጆችህ መካከል ትዋጀዋለህ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 13:13
7 Referencias Cruzadas  

ሙሴም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ጠርቶ አላ​ቸው፥ “ሂዱና በየ​ወ​ገ​ና​ችሁ ጠቦት ውሰዱ፤ ለፋ​ሲ​ካም እረ​ዱት።


ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ተና​ገሩ፤ በሉ​አ​ቸ​ውም፦ በዚህ ወር በዐ​ሥ​ረ​ኛው ቀን ሰው ሁሉ ለአ​ባቱ ቤተ ሰቦች ቤቶች አንድ አንድ ጠቦት፥ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰውም ለራሱ ቤተ ሰብእ አንድ ጠቦት ይው​ሰድ።


“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ከሰ​ውም፥ ከእ​ን​ስ​ሳም መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ውን ማሕ​ፀ​ንን የሚ​ከ​ፍት በኵር ሁሉ ለእኔ ለይ​ልኝ፤ የእኔ ነው።”


የአ​ህ​ያ​ው​ንም በኵር በበግ ትዋ​ጀ​ዋ​ለህ፤ ባት​ዋ​ጀው ግን ዋጋ​ውን ትሰ​ጣ​ለህ። የል​ጆ​ች​ህ​ንም በኵር ሁሉ ትዋ​ጃ​ለህ። በፊ​ቴም ባዶ እጅ​ህን አት​ታይ።


ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos