ኤፌሶን 1:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉን ነገር በራሱ ፈቃድ የሚሠራ እግዚአብሔር አስቀድሞ በዐቀደልን መሠረት በክርስቶስ አማካይነት የእርሱ ወገኖች እንድንሆን መረጠን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉን በፈቃዱ ምክር መሠረት እንደሚሠራው እንደ እርሱ ዕቅድ፣ አስቀድሞ የተወሰንን እኛ ደግሞ በርሱ ተመርጠናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ፈቃዱና እንደ ምክሩ ሁሉን የሚያከናውን እንደ እርሱ ዓላማ የተወሰንን በክርስቶስ በርስትነት ተቀበልን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ አስቀድመን የተወሰን በእርሱ ርስትን ተቀበልን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን። |
አምላክ ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ፤ አንተ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን አድርገሃል፤ ከጥንት ጀምሮ ያቀድከውን ሁሉ፥ ፍጹምነት ባለው አስተማማኝ ሁኔታ አከናውነሃል።
“እኛ በዐይናችን እናያት ዘንድ እግዚአብሔር ሊያደርግ ያቀደውን በፍጥነት ያድርግ፤ እናውቃትም ዘንድ የእስራኤል ቅዱስ ያቀዳት ምክር ትፈጸም” ለሚሉ ሁሉ ወዮላቸው!
ዓላማህ ታላቅ ነው፤ ሥራህም ኀያል ነው፤ ሕዝቦች የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ ታያለህ፤ ለእያንዳንዱም ሰው እንደአካሄዱና እንደየሥራው ዋጋውን ትከፍላለህ።
የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚመራ እርሱ ነው፤ የንጉሥነትን ክብር በመቀዳጀት በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ አንድ ካህን በዙፋኑ አጠገብ ይቆማል፤ ሁለቱም አብረው በስምምነትና በሰላም ይሠራሉ።’
እርሱም ራሱ እግዚአብሔር አስቀድሞ ባቀደውና ባወቀው አሠራር መሠረት ለእናንተ ተላልፎ ተሰጠ፤ እናንተም በዐመፀኞች እጅ እንዲሰቀልና እንዲሞት አደረጋችሁት።
ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’
እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን የእርሱ ወራሾች ነን፤ ከክርስቶስም ጋር እንወርሳለን፤ አሁን የክርስቶስ መከራ ተካፋዮች ብንሆን በኋላ የክብሩ ተካፋዮች እንሆናለን።
ይህም የሆነበት ምክንያት አስቀድሞ ያወቃቸው ልጁን እንዲመስሉና ልጁም ከብዙ ወንድሞች መካከል በኵር እንዲሆን እግዚአብሔር አስቀድሞ ስለ ወሰነ ነው።
አንድ ነገር የሚወረሰው በሕግ አማካይነት ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል አማካይነት መሆኑ በቀረ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ውርስን ለአብርሃም የሰጠው በተስፋው ቃል አማካይነት ነው።
ለምን ዐይነት ተስፋ እንደ ተጠራችሁና ቅዱሳን የሚወርሱት ክቡር ርስት ምን ያኽል ብዙ እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ የልቡናችሁ ዐይን እንዲበራላችሁ እጸልያለሁ።
እናንተ ግን እሳት እንደሚነድበት የብረት ምድጃ ከሆነችው ከግብጽ መንጥቆ እግዚአብሔር ያወጣችሁ ዛሬ እንደ ሆናችሁት ሁሉ ለራሱ የተለያችሁ ወገኖቹ እንድትሆኑ ነው።
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?