መክብብ 5:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብት ሲበዛ በዚያው መጠን በላተኛው ይበዛል፤ ታዲያ፥ አይቶ ከመደሰት በቀር ለባለቤቱ ምን የሚተርፈው ነገር አለ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብት በበዛ ቍጥር፣ ተጠቃሚውም ይበዛል፤ በዐይኑ ብቻ ከማየት በቀር ታዲያ፣ ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥቂትም በላ ብዙ፥ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው፤ የሀብታም ጥጋብ ግን እንቅልፍን ይከለክለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሀብት ሲበዛ የሚበሉት ይበዛሉ፤ በዐይኑም ከማየት በቀር ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሀብት ሲበዛ የሚበሉት ይበዛሉ፥ ሀብቱን በዓይኑ ብቻ ከማየት በቀር ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል? |
ወጣት ሆይ! ወጣትነት እጅግ ግሩም ስለ ሆነ በወጣትነትህ ዘመን ደስ ይበልህ፤ በልብህም ሐሤት አድርግ፤ ዐይንህ የሚያየውንና ልብህ የሚመኘውን ሁሉ ፈጽም፤ ሆኖም ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
የጉልበት ሥራ የሚሠራ ሰው ብዙም ሆነ ጥቂት ቢመገብ የሰላም እንቅልፍ አግኝቶ ያድራል፤ የባለ ጸጋ ሰው የሀብት ብዛት ግን ሀብቱ እንቅልፍ ይነሣዋል።
ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ሀብትን የሚሰበስብ፥ ያልጣለችውን ዕንቊላል ታቅፋ እንደምትፈለፍል ቆቅ ነው፤ በዕድሜው አጋማሽ የሰበሰበውን ሃብት ሁሉ ያጣል። በመጨረሻም ሞኝነቱ ግልጥ ይሆናል።