La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መክብብ 10:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰው ቤቱን ከመጠገን ቸል ቢል ጣራው ይዘብጣል፤ ክዳኑም ያፈሳል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰው ሰነፍ ከሆነ ጣራው ይዘብጣል፤ እጆቹም ካልሠሩ ቤቱ ያፈስሳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ተግባር በመፍታት ጣራው ይዘብጣል፥ በእጅም መታከት ቤት ያፈስሳል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሰ​ዎች ስን​ፍ​ናና ቦዘ​ኔ​ነት የቤት ጣራ ይዘ​ብ​ጣል፥ በእ​ጆች ስን​ፍ​ናም ቤት ያፈ​ስ​ሳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ተግባር በመፍታት ጣራው ይዘብጣል፥ በእጅም መታከት ቤት ያፈስሳል።

Ver Capítulo



መክብብ 10:18
8 Referencias Cruzadas  

በሥራ ትጉህ መሆን ገዢ ያደርጋል፤ ሰነፍ መሆን ግን ተገዢ ያደርጋል።


ጥበበኛ ሴት ቤትዋን በሥነ ሥርዓት ታስተዳድራለች፤ ሞኝ ሴት ግን በገዛ እጅዋ ታፈርሰዋለች።


መሬቱን በወቅቱ የማያርስ ሰነፍ ገበሬ በመከር ጊዜ የሚሰበስበው ምርት አይኖረውም።


መሥራት የማይፈልግ ሰነፍ ሰው ራሱን የገደለ ያኽል ይቈጠራል።


ሰካራሞችና ሆዳሞች ይደኸያሉ፤ ሙያው ማንቀላፋት ብቻ የሆነ ሰውም ደኽይቶ ቡትቶ ለባሽ ይሆናል።


እናንተ ሁላችሁም በተስፋ የምትጠባበቁትን ነገር እስክትጨብጡ ድረስ ትጋታችሁን እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን፤