ዘዳግም 9:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመዓቱም ሊደመስሳችሁ ስለ ተነሣሣ የእግዚአብሔር ብርቱ ቊጣ አስፈርቶኝ ነበር፤ ነገር ግን እንደገና እግዚአብሔር ልመናዬን ሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተን ሊያጠፋችሁ ክፉኛ ተቈጥቶ ነበርና፣ እኔም የእግዚአብሔርን ቍጣና መዓት ፈራሁ፤ እግዚአብሔር ግን እንደ ገና ሰማኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ሊያጠፋችሁ በመነሳቱ ከቁጣውና ከመዓቱ የተነሣ ፈራሁ። ጌታ ግን ልመናዬን ደግሞ ሰማኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ሊያጠፋችሁ ከተቈጣባችሁ ከቍጣውና ከመዓቱ የተነሣ ፈራሁ፤ እግዚአብሔርም በዚያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ። |
ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ሕዝቦቹን ለማጥፋት ዐቅዶ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የመረጠው ሙሴ በመካከል በመቆም፥ እንዳያጠፋቸውና ቊጣውንም እንዲመልስ እግዚአብሔርን ለመነ።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚህ በፊት በምድር ላይ በማንኛውም ሕዝብ ዘንድ ሆኖ የማያውቅ ድንቅ ነገር በሕዝብህ ፊት አደርጋለሁ፤ አስፈሪ የሆነ ድንቅ ነገር ስለማደርግ እኔ እግዚአብሔር የማደርጋቸውን ድንቅ ነገሮች በመካከላቸው የምትኖርባቸው ሕዝቦች ሁሉ ያያሉ።
“እኔም ከዚህ በፊት ባደረግሁት ዐይነት እንደገና በተራራው ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በመጸለይ ቈየሁ፤ እግዚአብሔርም እንደገና ልመናዬን ሰምቶ አንተን ላለማጥፋት ፈቀደ።
ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ይቈጣል፤ ሰማያትን ዘግቶ ምድሪቱን ዝናብ እንዳይዘንብባትና ፍሬ እንዳትሰጥ ያደርጋል፤ እናንተም እግዚአብሔር ከሚሰጣችሁ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ።