ሁልጊዜ በዚህ ዐይነት ቢያስቡማ እንዴት መልካም ነበር! ሁልጊዜ ቢያከብሩኝና ትእዛዞቼንም ሁሉ ቢፈጽሙ ሁሉ ነገር ለእነርሱና ለዘሮቻቸው ለዘለዓለም በመልካም ሁኔታ በተከናወነላቸው ነበር።
ዘዳግም 5:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁንም ሂድና ወደየድንኳናቸው እንዲመለሱ ንገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሄደህ ወደየድንኳናቸው እንዲመለሱ ንገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም ሂድና፦ “ወደ ድንኳናችሁ ተመለሱ” ብለህ ንገራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄደህ፦ ወደ ቤቶቻችሁ ተመለሱ በላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሄደህ፦ ወደ ድንኳናችሁ ተመለሱ በላቸው። |
ሁልጊዜ በዚህ ዐይነት ቢያስቡማ እንዴት መልካም ነበር! ሁልጊዜ ቢያከብሩኝና ትእዛዞቼንም ሁሉ ቢፈጽሙ ሁሉ ነገር ለእነርሱና ለዘሮቻቸው ለዘለዓለም በመልካም ሁኔታ በተከናወነላቸው ነበር።
አንተ ግን እዚህ እኔ አጠገብ ቁም፤ እኔም ሕግጋቴን፥ ትእዛዞቼንና ሥርዓቶቼን ሁሉ እሰጥሃለሁ፤ እኔ በምሰጣቸው ምድር እነዚህን ሕግጋቴን፥ ትእዛዞች ሥርዓቶቼን በመጠበቅ እንዲኖሩ ለሕዝቡ አስተምራቸው።’